የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስራውን አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተተው የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር አስታወቀ።የውጪ ምንዛሪ እጥረት ለተሽከርካሪ ማንቀሳቀሻ የሚያስፈልጉኝን ግብአ…

የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስራውን አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተተው የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር አስታወቀ።

የውጪ ምንዛሪ እጥረት ለተሽከርካሪ ማንቀሳቀሻ የሚያስፈልጉኝን ግብአቶች እንዳልገዛ አድርጎኛል ሲል ማህበሩ አስታውቋል።

የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጸጋ አሳመረ በጉዳዩ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።

አቶ ጸጋ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በሀገሪቱ የተፈጠረው የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት እጥረት ለተሽከርካሪ ማንቀሳቀሻ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ዋና አንሮታል ብሏል።

20 በመቶ ተሽከርካሪዎቹም የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት ባስከተለው ጉዳት ምክንያት በጋራዥ መቆማቸውን ገልጿል።

የአገልግሎት መስጫ የታሪፍ ማስተካከያም በጥናት ተመርኩዞ ስለማይደረግ ዘርፉን ለኪሳራ እንደዳረገውም ተናግረዋል።

ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የአገልግሎት መስጫ ታሪፍ በየስድስት ወሩ እንዲወሰን መግባባት ላይ ቢደርስም ተግባራዊ እንዳልሆነም ሰብሳቢው ገልጸዋል።

ከ2008 እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ ባሉት ዓመታት የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ላይ የ58% የዋጋ ጭማሪ ታይቷል።

ይህም በዘርፉ ከሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከ20 በመቶ በላይ ከስራው ውጭ ሆነው በጋራዥ እንዲቆሙ ተገደዋል ተብሏል።

ሌሎች ደግሞ በወር ከአንድ ጊዜ በላይ መስራት እንዳልቻሉ በመግለጫው ተጠቁሟል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply