የውጭ የምግብ አቀነባባሪ ኩባንያ ፍላጎት በማሳየቱ የሽሮ ወጥ ደረጃ መዘጋጀቱ ተገለጸየውጭ አገር የምግብ አቀናባሪ ኩባንያ ሽሮ ወጥን በኢትዮጵያ ውስጥ በፋብሪካ ደረጃ አዘጋጅቶ ለማቅረብ ፍላጎ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/JMR_Lt6Iy9pzg3TRXPRKW_1sQhVhdWQMCMOx674Uee2GZ33PUtPy9i91keJubZ2T_vpoapCFsAKYbHZWQXS2c_b7dednMC3m3_XBajBfXxxMZgyYcFHwJ3YKczvo2rEx4YQNuWMnt0sktaQz8kElhU3IO1UBTuJDPQx6liC7Dx1L44Xfrz6Hszmb23aMYBA4MH5XYufVSfiyHTvNNoUvOCTXFpWGNtH4LSB6QPuEDoJ6tsSpc-sG0akF3zelTHLKxZ_mszkF4CE6tR0OZ5eX1oBJPIxsmCExE_5RVqXI5A5DKcy0495jUEwN2FTXGPwHqANfusxIPc0lS5SRLhLDyQ.jpg

የውጭ የምግብ አቀነባባሪ ኩባንያ ፍላጎት በማሳየቱ የሽሮ ወጥ ደረጃ መዘጋጀቱ ተገለጸ

የውጭ አገር የምግብ አቀናባሪ ኩባንያ ሽሮ ወጥን በኢትዮጵያ ውስጥ በፋብሪካ ደረጃ አዘጋጅቶ ለማቅረብ ፍላጎት መኖሩን ተከትሎ የሽሮ ወጥ ደረጃ ማዘጋጀት ማስፈለጉን የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ገለጸ።

ኢንስቲትዩቱ ከሽሮ ወጥ በተጨማሪ ወደ ውጭ አገራት የሚላኩ የተለያዩ “አገር በቀል ምርቶችን” የምግብ ደኅንነት እና የምርቱን ምንነት እና ይዘት ለማሳወቅ ደረጃዎች እያወጣ መሆኑንም አመልክቷል።

ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን መሠረት በማድረግ የምግብ ይዘታቸው ላይ ጥናት ተደርጎባቸው ደረጃቸው ወጥቷል የተባሉ ምርቶች ሽሮ፣ በርበሬ፣ በሶ እና ጠጅን ያካትታል።

ባለፈው ዓመት ደረጃቸው የወጣላቸው የምግብ ምርቶቹ “ፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ” ቁጥጥር የሚደረግባቸው ሲሆን፣ ደረጃቸውም አስገዳጅ አለመሆኑን ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።

የሽሮ ዱቄት ደረጃ ሦስት ክፍሎችን የያዘ መሆኑን የተናገሩት የኢንስቲትዩቱ የደረጃዎች ዝግጅት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ይልማ መንግሥቱ፤ የምግብ ይዘቱን እና እርጥበቱን፣ ሲፈጭ እና ሲታሸግ ያለው ንክኪ እንዲሁም በእሽጉ ላይ ምንነቱን እና የመጠቀሚያ ጊዜውን የሚይዝን መግለጫ ያካተተ ነው ብለዋል።

የማኅበረሰቡ አኗኗር እየተለወጠ በመሆኑ ሽሮን ከማዘጋጀት ይልቅ መግዛት በመለመዱ ደረጃውን ማውጣት “ወሳኝ” እንደሆነም ኃላፊው ገልጸዋል።

የራሱ የሆነ ምግብ ሂደትን አልፎ እና ተጨማሪ ግብዓቶችን ተጠቅሞ ለምግብነት የሚውለው ሽሮ ወጥም ጥራቱ እና ደኅንነቱ እንዲጠበቅ ደረጃ እየተዘጋጀለት መሆኑንም አስረድተዋል።

ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply