የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አማባሳደር ማይክ ሬይነርን በጽ/ቤታቸው አስጠርተው ማብራሪያ ጠየቁ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አማ…

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አማባሳደር ማይክ ሬይነርን በጽ/ቤታቸው አስጠርተው ማብራሪያ ጠየቁ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አማባሳደር ማይክ ሬይነርን ዛሬ በጽ/ቤታቸው አስጠርተው አነጋግረዋቸዋል፡፡

አቶ ገዱ አምባሳደሩን ያስጠሯቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የህዳሴ ግድብን አስመልክተው በሰጡት አወዛጋቢ አስተያየት ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡ ነው፡፡

ትረምፕ አወዛጋቢውን አስተያየት የሰጡት ከሱዳን እና ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ጋር የቴሌፎን ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

አቶ ገዱ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ፕሬዝዳንት ትረምፕ በግድቡ እና በሶስትዮሽ ድርድሩ ዙሪያ የሰጡት አስተያየት የተሳሳተ ነው፡፡

ፕሬዝዳንቱ ግድቡ የናይል ወንዝን የውሃ ፍሰት ያቆመዋል ነው ያሉት፤ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም ብለዋል አቶ ገዱ፡፡

በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ጦርነት ማወጅ በስልልጣን ላይ ካለ አንድ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሚጠበቅ አይደለም፡፡

በኢትዮጵያእና በአሜሪካ መካከል የቆየውን ወዳጅነት እና ስትራቴጂያዊ አጋርነትም አይመጥንም ብለዋል አቶ ገዱ፡፡

የመንግስታት ግንኙነትን በሚገዛው ዓለም አቀፍ ሕግም ተቀባይነት የለውም ነው ማለታቸውን ኢትቪ ዘግቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply