You are currently viewing የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ዎህዴግ የአቋም መግለጫ፦ ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 10/2014 ዓ.ም          አሻራ ሚዲያ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎህዴግ…

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ዎህዴግ የአቋም መግለጫ፦ ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 10/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎህዴግ…

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ዎህዴግ የአቋም መግለጫ፦ ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 10/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎህዴግ) የዎላይታ ሕዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር የዘመናት ሕገመንግሥታዊ ጥያቄ ፍጹም ሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ተክትሎ እያስኬደ ባለበት ወቅት በአንጻሩ ኢ ህገመንግሥታዊ የክላስተር አወቃቀርን በተመለከተ ያለንን ቅሬታ ለኢትዮጵያ ፌድረሽን ም/ቤት በዋናነት እንድሁም ለአሜሪካ ኤምባሲ፣ለኢንግሊዝ ኤምባሲ፣ ለኢትዮጵያ ሰበኣዊ መብት ጉባኤ እና ለኢትዮጵያ ጠበቆች አሳውቀናል። ግንባሩ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ የሕዝቡን ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱን እስኪጎናጸፍ ድረስ የሚናደርገውን ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን የሚንቀጥል መሆናችንን አጥብቀን እየገለጽን የቅሬታ ደብዳቢያችንን ሙሉ ነጥቦችን እንደሚከተለው አቅርበናል። 1. እንደሚታወቀው የዎላይታ ህዝብ ህገ መንግስታዊ፣ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ መነሻዎች ታሳቢ በማድረግ በአገራዊና አከባቢያዊ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መስተጋብሮች ዙሪያ ያለፈዉን ፍትሀዊና ድርሻ የሚያጎለብትበትን ነገር ግን ኢ-ህገ መንግስታዊ በሆነ መንግድ ከሽግግር ወቅት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ምላሽ ያላገኘውን የራስን ክልል የመመስረት ህገ መንግስታዊ መብት በ370 ቀበሌ ምክር ቤቶች፣ በ22 ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ም/ቤቶች እና በወሊይታ ዞን ምክር ቤት በዴሞክራሲያዊ መንገድ መክሮና ተወያይቶ በሙለ ድምጽ አፅድቆ ወደ ደቡብ ክልል ም/ቤት ታህሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ህዝበ ዉሳኔ እንዲደራጅ መላኩ ይታወሳል፡፡ 2. ይሁን እንጂ በኢፈዴሪ ህገ መንግስት መግቢያ፣ አንቀጽ 8፣ 25፣39፣46 እና 47 (3) ሊይ በማያሻማ ሁኔታ በተቀጠሙት መንግስታት በሀገራችን ህዝቦች ሊይ ስደርስ የነበረዉን ታሪካዊ፣ ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ኢ-ፍትሀዊነቶችን እና ጭቆናዎችን ማረም እና መካስን ታሳቢ በማድረግ ለሁለም ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች በዕኩልነት እንዲተገበሩ የተደነገጉ ህገ መንግስታዊ መብቶችን በሚጣረስ መልክ በህዝቦች መካከል ያለዉን ዕኩልነት እና በሀገርቷ ያሆነዉን የህግ የበላይነትን ወደ ጎን በማድረጎ የደቡብ ክልል ምክር ቤት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 47/3/ በተቀመጠው መሠረት ህዝበ ዉሳኔ ማዘጋጀት ሲገባዉ የዎሊይታን ብሔር ጥያቄ ኢ-ህገ መንግስታዊ እና ኢ-ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልክ በማፈኑ የዎላይታ ዞን ምክር ቤት በቀን 11/04/2012 ዓ.ም ለተከበረዉ ፋዴሬሽን ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 251/93 አንቀጽ 19(3(2)) መሠረት በተሰጠዉ ሥልጣን የክልል ምክር ቤት ከህገ መንግስታዊ አሠራር ዉጭ ያጸደቀዉን የራስን ክልል የመመስረት ጥያቄ በህዝበ ዉሳኔ እንዲመለስ አቤቱታ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ 3. የተከበረዉ ፋዴሬሽን ምክር ቤት የዎላይታ ብሔር በክልል የመደራጀት ጥያቄ በይግባኝ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ በጥናት መልሳለሁ እያለ ህገ መንግስታዊ ምሊሽ ሳይሰጥ በአዋጅ ቁጥር 251 አንቀጽ 19(3 (3)) የተቀመጠዉ የ2-ዓመት ጊዜ ገደብ ታህሳስ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ማለፉ ይታወቃል፡፡ 4. በሌላ በኩል የደቡብ ክልል እና የፈዴራል መንግስት የህገ መንግስታዊ ጥያቄ ፖለቲካዊ ምሊሽ በጥናት እና በ80ዎች ኮሚቴ በኩል ከሌሎች ብሔሮችና ብሔረሰቦች ጋር በማጣመር ነባሩን የደቡብ ክልል በአራት ወይም በአምስት ክልሎች የማዋቀር አደረጃጃት በመፌጠር የተደረገዉ ሙከራ በየአከባቢዉ ከፍተኛ ተቃዉሞ በማስነሳቱ ልከሽፍ ችሏል፡፡ 5. ይህ በእንዲህ እዳለ 23 ቀን 2014 ዓ.ም የዎላይታ ዞን ምክር ቤት ያደረገው የህዝብ ምክክርና ዉይይት ከዚህ በፉት በክልል ለመደረጃት በህዝብ እንዴራሴነት ያቀረበዉን ጥያቄ በገዥዉ ፖለቲካ ፓርቲ አቅጣጫ መሠረት ከለሎች 10 አጎራባች መዋቅሮች ከሚኖሩ ህዝቦች ጋር በክሊስተር እንደራደራጁን በማለት ወስኖ ለተከበረዉ ፈዴሬሽን ምክር ቤት መላኩን ፓርቲያችን እንደማንኛዉም ወገን በሚዲያ ሰምተናል፡፡ 6. ይሁን እንጂ የዎሊይታ ብሄርን መሰረት አድርጎ እንደተመሰረተ የፓለቲካ ፓርቲ የዎሊይታ ህዝብን ቀጣይ የአስተዳደር፣የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እጣ ፊንታ በሚወስን መሰረታዊ ህገ መንግስታዊ ጥያቄ በሚመለስበት አግባብ ምንም ዓይነት በአከባቢዉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክርና ዉይይት ሳይደረግ ከህገ መንግስታዊ መርህ እና ከህዝቡ ፌላጎት ዉጪ በጥቂት የገዥ ፓርቲ ተወካዮች በኩል የህዝቡ የዘመናት ህገ መንግስታዊ ጥያቄ ለመመለስ እየተከሄደበት ያለዉ ሁኔታ ላይ የሚከተለዉን የአሠራርና ህገ መንግስታዊ ጥሰት ስለተገነዘብን እንዲስተካከል እናቀርባለን፡፡ 7. የዎላይታ ዞን ምክር ቤት በፈዴሬሽን ምክር ቤት በህጋዊ መንገድ ምላሽ ለመስጠት በሂደት ላይ የሚገኘዉን የዎሊይታ ብሔር ራስን በራስ ክልል የመደራጀት ህገ መንግስታዊ ጥያቄ በራሱ ሰዓት የህዝብ ፌቃድ እና ስምምነት ሳያገኝ አስቸኳይ ጉባኤ ጠርቶ በድብቅ ከህዝብ ፌላጎት ዉጪ ያለ ህዝበ ዉሳኔ በክሊስተር እንድደራጅ የማድረግ ህገ መንግስታዊ ሥልጣን ሳይኖረዉ የሰጠዉ ዉሳኔ ስለሆነ ታርሞ ህዝበ ዉሳኔ እንዲድረግ እንጠይቃለን፡፡ 8. የዎላይታ ዞን ምክር ቤት ተወካዮች ለምክር ቤት አባልነት ከተመረጡ 9 ዓመት የሞላቸዉ እና የምርጫ ዘመናቸዉ ያለቀባቸዉ ስለሆኑ በብሔሩ ራስን በራስ ክልል የመደራጀት ህገ መንግስታዊ ጥያቄ በመጀመሪያ ደረጃ ዉሳኔ የመስጠት ሥልጣን የላቸዉም በመቀጠል ብኖራቸዉ እንኳን የምርጫ ጊዚያቸዉ ያበቃ ስለሆነ የሚሰጡት ዉሳኔም ህገ ወጥ ስለሚሆን የፈዴሬሽን ምክር ቤት ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብት በህዝበ ዉሳኔ ብቻ የሚተገበር መሆኑን በመገንዘብ እንዲደራጅ እንጠይቃለን፡፡ 9. የተከበረዉ ፈዴሬሽን ምክር ቤት የዎላይታ ዞን ምክር ቤት ከዚህ በፊት ከቀበሌ እስከ ዞን ምክር ቤት መላዉ ህዝብ ተሳትፎና አምኖ ያቀረበዉን የራስን ክልል የመመስረት ህገ መንግስታዊ ጥያቄ የኢፈዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 47 እና የፈዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣን ለመወስን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 251/93 አንቀጽ 19(3(2)) መሰረት በአሁኑ ሰዓት በገዥ ፓርቲ ተወካዮች በኩል የሚቀርቡ በክላስተር የመደረጀት አማራጭ እና የዎላይታ ብሔር በራሱ ብቻዉን ክልሰ የመመሰረት አማራጭን በህዝበ ዉሳኔ መለየት ህገ መንግስታዊ አሠራር ከመሆኑም በላይ የለዓላዊ ሥልጣን ባለቤት ህዝቡ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ብቸኛ ህጋዊ መንገድ መሆኑን ፓርቲያችን በጽኑ የሚያምን ስለሆነ ህዝቡ በድምጽ ያላረጋገጠዉ የክላስተር አደረጃጃት ኢ-ህገ መንግስታዊ መሆኑን ተገንዝቦ ህዝበ ዉሳኔ እንዲደራጅ እንጠይቃለን፡፡ 10. ክብር የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲገነዘብ የሚንፈልገዉ የዎላይታ ብሔር በኢፌዴሪ ህገ መንግስት የተቸረዉን በክልል መዋቅር የመመስረት ጥያቄ በሽግግር ወቅት በክልል-9 ከተደረጀበት በኋላ በኢ- ፍትሀዊ መንገድ ወደ ደቡብ ክልል ተጨፌልቆ እንዲዋቀር ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ የራስን ታሪክ፣ማንነት፣ባህል እና ቋንቋ የሚያሳድግበት ከሀገራዊ ግዴታዉ በተጨማሪ እየየጠየቀ የቆየ ህዝብ ነዉ፡፡ 11. ለአብነትም በ1992 ዓ.ም ጥቅምት ወር በዎላይታ ሶዶ ከተማ እና አጎራባች ወረዳዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የብሔሩ ተወላጆች በጥቂት የፓለቲካ ልህቃን የህዝቡን ማንነት የሚጨፍልቅ አሪተፍሻል “ወጋጎዳ” የተሰኘ ቋንቋ በሥርዓተ ትምህርት ቀርፆ በማምጣታቸዉ መነሻ “ወጋጎዳ አንማርም፣ ባህሌና ቋንቋዬ ይከበር ፣ ክልልነት ይሰጠን ” በሚል አደባባይ ወጥቶ ህዝባዊ ተቃዉሞ በማድረግ መስዋዕትነት ከፍል የኢፈዴሪ ህገ መንግስት እንዲከበር ፋና ወጊ ሚና በመጫወት ቋንቋን ማስጠበቅ የቻለ ብሆንም ምንም እንኳን ክልልነት ቢጠየቅም በወቅቱ በዞን መዋቅር በማደረጃት ጥያቄዉን በከፊል መልሶ ህዝቡን ማረጋጋት እንደተቻለ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነዉ ፡፡ 12. የዎላይታ ብሔር በክልል የመደራጀት ጥያቄ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ በዘመነ ኢህአዴግ ጊዜ ከላይ እንዳመለከትነው ተጠናክሮ ሲቀርብ የነበረ እና ሀገራዊ ለዉጡን ተከትሎ በተፈጠረዉ ሀገረ መንግስት ግንባታ የዎላይታ ህዝብ ከዚህ በፊት በነበረዉ የጋራ አደረጃጃት ስደርሰበት የነበረዉ ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ጭቆና አንገሽግሾ ከህፃን እስከ አዋቂ ድረስ የጋራ ስምምነት ላይ ተደረሶ የቀረበ የዘመናት ጥያቄ መሆኑን እና ባለፉት 4 የለዉጥ አመታት ህዝቡ በሠላማዊና ህገ መንግስታዊ መንገድ ጥያቄዉን እያቀረበ የቆየ መሆኑን ፌዴሬሽን ምክር ቤት በመገንዘብ በህገ መንግስታዊ መንገድ ህዝበ ዉሳኔ በማድረግ ህዝቡ ምርጫዉን እንዲወስን እንዲደረግ እንጠይቃለን ። 13. በመጨረሻ የተከበረዉ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በህገ መንግስቱ እና በአዋጅ ቁጥር 251/93 መሰረት በተሰጠዉ ሥልጣን ከሀገራችን ብሔረ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ስቀርብ ህገ መንግስታዊ መርህ ተከትሎ ለሁለም ህዝቦች በዕኩልነት ፍትሀዊ ምላሽ የመስጠት ህገ መንግስታዊ አደራ ያለበት ተቋም መሆኑን ፓርቲያችን በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረቡ ህዝቦች ምርጫቸዉን በህዝብ ዉሳኔ በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲያሳዉቁ በዕኩልነት በሲዳማ ብሔር እና የደቡብ ምዕራብ ክልሎች ስዋቀሩ የተተገበረዉ ህዝበ ዉሳኔ የማደረጃት ህገ መንግስታዊ አሠራር ለዎላይታ ብሔር ጥያቄም እንዲተገበር እንጠይቃለን፡፡ ማጠቃለያ ############################## የዎላይታ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ህገመንግስታዊ፣ ሰባአዊ እና ታሪካዊ መብቱን በሀገርቱ ህገመንግስት አንቀጽ 9 ላይ እንደተደነገገው ማንኛውም ህገመንግስቱ የሚቃረን አዋጅ፣ ልማዳዊ አስራር እንድሁም የፖለቲካ ጫና ተፈፃሚነት አይኖረውም ይላል። የዎላይታ ሕዝብ ራስን እድል በራስ የመወሰን ስልጣንና መብት ያጎናጸፈው የኢፌዴሪ ህገመንግስት በመሆኑና ክላስተር የሚባል በህገመንግስቱ የማይታወቅና በህግ ድጋፍ የሌለው በመሆኑ ታላቁ የዎላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት መብቱ ተጠብቆ በሀገርቱ እኩል ውክልናና ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጥ በአስቸኳይ ህዝበ-ውሳኔ ተደርጎ የሚበጀውን ህዝቡ ራሱ እንዲወስን እድል መስጠት ህገ መንግስታዊም ሞራላዊም በመሆኑ የህዝቦች ህጋዊና ህገመንግስታዊ መብት በህዝበ ውሳኔ መቋጫ እንድያገኝ ሁሉም የድርሻውን እንድወጣ ዎሕዴግ ያሳስባል። የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር ነሐሴ 10/12/14 ዓም ወ/ሶዶ ኢትዮጵያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply