You are currently viewing “የዐማራ ሕዝብ ልዩ ኃይልን ማፍረስና ፋኖን ማሳደድ ዐማራን ለማጥፋት የተሸረበ ሴራ እንደሆነ መረዳት ይገባል!”…በመሆኑም የዐማራ ህዝብ፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ እየተናበበ ራሱን ከመጥፋ…

“የዐማራ ሕዝብ ልዩ ኃይልን ማፍረስና ፋኖን ማሳደድ ዐማራን ለማጥፋት የተሸረበ ሴራ እንደሆነ መረዳት ይገባል!”…በመሆኑም የዐማራ ህዝብ፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ እየተናበበ ራሱን ከመጥፋ…

“የዐማራ ሕዝብ ልዩ ኃይልን ማፍረስና ፋኖን ማሳደድ ዐማራን ለማጥፋት የተሸረበ ሴራ እንደሆነ መረዳት ይገባል!”…በመሆኑም የዐማራ ህዝብ፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ እየተናበበ ራሱን ከመጥፋት እንዲከላከል ሲል ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት (ሞወአድ) አፅንኦት ሰጥቶ ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት (ሞወአድ) በወቅታዊ ጉዳይ የሰጠው ሙሉ መግለጫ:_ የዐማራ ሕዝብ ልዩ ኃይልን ማፍረስና ፋኖን ማሳደድ ዐማራን ለማጥፋት የተሸረበ ሴራ እንደሆነ መረዳት ይገባል! የኦሮሙማው ገዥ ለ 5 አመት ገዳይና አፈናቃይ ሰራዊት አሰማርቶ፣ የአማራን ህዝብ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በወለጋ በአዲስ አበባና በመሳሰሉት በአሰቃቂ ሁኔታ እያፈናቀለና የዘር ጭፍጨፋ እያካሄደ መቀጠሉ የአደባባይ ሀቅ ነው። እንደ አጣየ ያሉትን ከተሞች በተደጋጋሚ እንዲወድሙ በማድረግ የኦሮሙማ አገዛዝ የአንበሳውን ድርሻ ወስዶ ሰርቷል። በሌላ በኩል ኦሮሙማ ከትግሬ ወያኔ ጋር በመተባበር በከፈቱብን ጦርነት 2 አመት ሙሉ የዐማራ ህዝብ ሰለባ ሆኗል። ሴቶች ተደፍረዋል፤ ቤተ እምነቶች ተቃጥለዋል፣ የከተማውንም የገጠሩም ንብረት ተዘርፏል። በአጠቃላይ በጦርነቱ በጎንደር በወሎ እስከ ሰሜን ሸዋ ያሉ ከተሞች እንዲወድሙ ተደርጓል። በወያኔና በኦሮሙማ ጥቃትና ውድመት ከፍተኛና ተደራራቢ ጉዳት የደረሰባቸው የዐማራ ተወላጅ ተፈናቃዮች ቁጥር በሚሊዮን የሚቆጠር እንደሆነ የዐይን እማኞች ይመሰክራሉ። እነዚህ በጨካኞች ግፍ የደቀቁ ተፈናቃዮች ወላጅ አልባ ህፃናት፣ እናቶች፣ አቅመ ደካማ ህሙማንና ጠዋሪ ቀባሪ የሌላቸው አረጋውያን በሀዘን፣ በርሀብና በልብ ስብራት ተጎሳቁለው የዕለት ጉርስ ለማግኘት የሰው እጅ የሚያዩ ተመፅዋቾች እንዲሆኑ ተደርጓል። “አውቆ የተደበቀ ቢጠሩት አይሰማም” እንዲሉ ይህ ሁሉ በደል ሲደርስ መንግሥት እንደመንግሥት ግፉ እንዲቆምም ሆነ ተጎጅዎቹ የስነልቦናም ሆነ የኢኮኖሚ ድጋፍ እንዲደርሳቸው አንዳችም ነገር አላደረገም። ይህን አሰቃቂ መከራ ለመቋቋም ሙከራ ያደረገው የዐማራ ልዩ ኃይልና የፋኖ ውለታ ከዐማራ ህዝብ ልብ ውስጥ የሚወጣ አይደለም። አገራችን ኢትዮጵያ በጎሳ ተሸንሽና፣ ሁሉም የራሱን ክልል ልዩ ኃይል አደራጅቶ በተለይም የኦሮሞ ክልል ልዩ ኃይል የመከላከያ ሰራዊት ማሰልጠኛ ተቋሞችን እየተጠቀመ፣ ከመከላከያ የሚስተካከል መጠን፤ ስልጠናና ትጥቅ እያለውና ኢትዮጵያን ለመሰልቀጥ አሰፍስፎ እየጠበቀ ባለበት፤ ወያኔ ትጥቅ ሳይፈታ ተጨማሪ ኃይል እያሰለጠነ እንደሆነ እየታወቀ፣ የዐማራ ልዩ ኃይል ይፍረስ ማለትና ፋኖን ማሳደድ፤ የዐማራን ህዝብ ከምድረ ገፅ ይጥፋ ብሎ እንደማወጅ የሚቆጠር አደገኛ አመጣጥ ነው። ነፃነት በልመና አይገኝምና ዐማራ ትጥቁን ከፈታ እስካሁን ከሆነበት ሁሉ የከፋ ማንነትንና እምነትን የሚያጠፋ፣ አገርን የሚያሳጣ ከፍተኛ አደጋ እንዳንዣበበት ተረድቶ ነፃነቱን ለማስከበር የማንንም ፈቃድ መጠየቅ የለበትም። በኦሮሚማ የዘር አጥፊ አገዛዝ ለአማራው ያለውን ጥላቻ በማያሻማ መልኩ አሳይቷል። በተለይ የአማራ ልዩ ኃይል አባልነት፣ የፋኖ አባልነት፣ በአጣቃላይ የአማራ ወጣትነት የአብይ መንግስት ልዩ ጠላቶች ሆነዋል። ሽመልን ጨምሮ የነፍስ ወከፍ የራስ መከላከያ አንዳይኖረው የተደረገ የአማራ አርሶ አደር ቤተሰቦች ሳይቀሩ በአጣዬ፣ በወለጋ፣ በመተከል፣ ውዘተ መንግስታዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው በሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ታጣቂዎች መጨፍጨቻቸውን ያየ የአማራ ልዩ ኃይልም ሆነ ፋኖ ትጥቅ መፍታትን ምርጫ ሊያደርገው አይችልም። ለዚህ ብአዴንና በፌደራል መንግስቱ ውስጥ ተሰግስገው በአማራ ስም የሚነግዱ የአብይ አህመድ ተላላኪዎች አጋዥነት የአማራ ልዩ ኃይልን የማፍረስ ሸፍጥ ውሳኔ በአማራው ህዝባዊ እንቢተኝነት መክሸፍ አለበት። እያንዳንዱ የአማራ ልዩ ኃይል አስረግጦ ማወቅ ያለበት፣ የወያኔ እና የኦሮሚማ አማራን የማንበርከክ ጣምራ ወረራ ከፊታችን ተጋርጦ በገሀድ እየታየ ባለበት ሁኔታ፤ ትጥቅ መፍታት ማለት የእራስን፣ የቤተሰብን እና የወገንን የመኖር ዋስትና ወይም ህልውና አሳልፎ መስጠት መሆኑን ነው። ስለዚህ የዐማራ ህዝብ፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ እየተናበበ ራሱን ከመጥፋት እንዲከላከል ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አፅንኦት ሰጥቶ ያሳስባል። አማራ በትግሉ ህልውናውን በኢትዮጵያ ያስከብራል!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply