የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የጠራውን አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደግፉ የገለፁት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የዐማራ ኮምኒቲ ማህበራት እና ሲቪክ ድርጅቶች መላ አማራ ብሎም ኢ…

የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የጠራውን አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደግፉ የገለፁት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የዐማራ ኮምኒቲ ማህበራት እና ሲቪክ ድርጅቶች መላ አማራ ብሎም ኢ…

የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የጠራውን አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደግፉ የገለፁት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የዐማራ ኮምኒቲ ማህበራት እና ሲቪክ ድርጅቶች መላ አማራ ብሎም ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሰልፉን እንዲቀላቀሉ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ እና የአለም አቀፉ የዐማራ ህዝብ ንቅናቄ አካል የሆንን የኮምኒቲ ማህበራት እና ሲቪክ ድርጅቶች የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የዐማራ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን መንግስት መር እና ስርዓታዊ የዘር ጭፍጨፋ ለመቃወም የጠራውን አለም አቀፍ ህዝባዊ ሰልፍ እንደምንደግፍ ፤ ለተግባራዊነቱም የድርሻችንን እንደምንወጣ እንገልፃለን ሲሉ አስታውቀዋል። የአለም አቀፉ ማህብረሰብ ስለዐማራ ህዝብ ትግል እና ከነገ ጀምሮ በሚደረገው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተገቢዉ ግንዛቤ እንዲኖረው ፤ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች እና የዜና አውታሮች ስለሰልፉ የዘገባ ሽፋን እንዲሰጡት አሳስበዋል። የአሜሪካን መንግስት ጨምሮ የሌሎች አገራት መንግስታት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በአግባቡ እንዲገነዘቡት እና በዐማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ጭፍጨፋ ለማስቆም የሚደርገውን ትግል እንዲደግፉ ድምፃችን በማሰማት በኩል አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናልም ብለዋል። ሆኖ የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን የጠራውን አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ አስመልክቶ ለልዩ ልዩ አካላት የሚከተለውን ጥሪ እናቀርባለን:- ፩. በአገር ውስጥ ለምትገኘው የዐማራ ህዝብ በተለይም ለዐማራ ወጣት:_ ልክ እንደትናንቱ ዛሬም እጅ አልሰጥም ብለህ ለህልውናህ እና ለነፃነትህ የምታደርገውን ፈታኝ ትግል በውጭ እንደሚኖር ወገንህ በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ምንግዜም ከጎንህ መሆናችንን እናረጋግጥልሃለን። ነፃነት በችሮታ የምትገኝ ሳትሆን በሚፈልጋት አካል ቆራጥ ትግልና ጥንካሬ የምትገኝ መሆኗን ትናንት ህወሓት መራሹን መንግስት ለማዳከም ያደረግከው የተግባር ትግል ፤ የከፈልከውም መስዋትነት ህያው ምስክር ነው። ትናንት ባደረግከው ትግል ነፃ ወጥቶ ራሱንም ህዝባችንንም ለዳግም ውርደት እና ባርነት ለዳረገው ብአዴን ፤ ነፃነት በትግል የሚገኝ እንጂ በችሮታ የሚሰጥ ነገር አለመሆኑን ፤ የማንንም መልካም ፍቃድ ሳትጠብቅ ድምፅህን በማሰማት በተግባር እንደምታሳይ እንተማመናለን ብለዋል። ፪. ለፀጥታ መዋቅር አባላት ፣ለልዩ ኃይል አባላት ፣ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ነገ ድምፁን ሊያሰማ የሚወጣው ወገንህ ሰላማዊ ተቃውሞውን የሚያሰማበት ምክንያት ያንተም ፣ ያንችም የሁላችንም ጉዳይ መሆኑን አስታውስ/አስታውሽ። በፀጥታ ማስከበር ስም በ2008 ዓ.ም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ለመግለፅ በወጡ ንፁሃን ዐማራዎች ላይ የተፈፀመው ጭፍጨፋ እንዳይደገም ፤ ወገኖቻችሁን ግደሉ ብለው ትዕዛዝ ለሚሰጧችሁ አካላት እምቢታችሁን በመግለፅ ፤ ለጩኸት ከሚወጣው ህዝብ አብራክ የተገኛችሁ እና ተልዕኳችሁም የአገርን እና የህዝብን ደህንነት መጠበቅ ስለሆነ ይህንኑ በተግባር እንድታሳዩ እናሳስባለን። ፫. ከአገር ውጭ ለምትኖረው ዐማራ እና የዐማራ ህዝብ ወዳጅ ሁሉ:_ በአገር ቤት ከነገ ዕረቡ ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሚደረገው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ድጋፋችንን ለማሳየት እና በሰላማዊ ሰልፉ የሚንፀባረቁ ህዝባዊ መልዕክቶችን ለመላው አለም ለማስተጋባት በተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ከተሞች በምንጠራቸው የሰላማዊ ሰልፎች እና ልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች በንቃት በመሳተፍ ኢትዮጵያ ውስጥ በዐማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን መንግስት መር እና ስርዓታዊ የዘር ጭፍጨፋ በፅኑ እንድታወግዙ እንጠይቃለን። የሰላማዊ ሰልፎቹ መረሃ ግብር ቀንና ተያያዥ ዝርዝር ጉድዯችን በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል። ፬. ለመላው ኢትዮጵያዊያን:_ የዐማራ ህዝብ በማንነቱ ተለይቶ በህይወት የመኖር ተፈጥሯዊ መብቱን ተከልክሎ በተገኘበት ቦታ ሁሉ ኢ-ሰባዊ በሆነ ሁኔታ ሲጨፈጨፍ ፤ ድርጊቱን ለመቃወም ሰው መሆን በቂ ሰለሆነ ፤ ከዛም በላይ አገር የሚባለው ፅንሰ ኃሳብ ያለህዝብ ከንቱ መሆኑን በመገንዘብ የዐማራ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን ስርዓታዊ የዘር ጭፍጨፋ ለመቃወም የሚያደርገውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በመቀላቀል እንደሰው ፤ እንደህዝብ እና እንደአገር የሚያስተሳስረንን ምክንያት እንድታሳዩን እንጠይቃለን። የዐማራ ህዝብ በልጆቹ ትግል ነፃነቱን ይመልሳል!! 1. ሲያትል የዐማራ ማኅበር 2. ነፃ የአማራ ማህበር በቨርጂንያ 3. የአማራ ህብረተሰብ ቅርስ በሚኒሶታ 4. የአማራ ማህበር በሎስ አንጀለስ 5. የአማራ ማህበር በካሊፎርኒያ/ሳንድያጎ 6. የአማራ ማህበር በኔቫዳ 7. የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) 8. የአማራ ማህበር በካናዳ ለሰብአዊ መብት 9. የአማራ ማህበር -ኮሎራዶ 10. የአማራ ማህበር በጆርጂያ 11. የአማራ ባለሙያዎች ማህበር (አምባ) 12. የአማራ ማህበር በዳላሰ

Source: Link to the Post

Leave a Reply