የዐብይ አህመድ ኢትዮጵያን የመናድ የጭካኔ ጥግ !! ፀሀፊ ሀብታሙ አያሌው *********** በቤተክርስቲያን ላይ በግልፅ ወንበዴዎች ተሰማሩ !! —…

የዐብይ አህመድ ኢትዮጵያን የመናድ የጭካኔ ጥግ !! ፀሀፊ ሀብታሙ አያሌው *********** በቤተክርስቲያን ላይ በግልፅ ወንበዴዎች ተሰማሩ !! —————… ዐብይ አህመድ በኦሮሚያ በይፋ ከ20 በላይ ጳጳሳት ሾመ !! ————— የክፋቱ ልክ ሰይጣንን የሚያስንቀው ዐብይ አህመድ ቤተመንግሥት እየሰበሰበ ሲያወያያቸው ጥበቃና በጀት መድቦ ለዚህ የከፋ ተግባር ሲያዘጋጃቸው የነበሩትን በቤተክርስቲያን ላይ በክፋትና በድፍረት የተነሱ ቡድኖች አደራጅቶ ከሥርአተ ቤተክርስቲያን እና ከቀኖና ውጪ ዛሬ በኦሮሚያ ሀሮ ባለወልድ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው አቡነ ሳዊሮስ በመባል ይታወቁ በነበሩት ሰው መሪነት ከየቦታው የሰበሰቡትን ካድሬዎች በዐብይ አህመድ ትዕዛዝ ጳጳስ ብለው በይፋ ሹመት ሰጥተዋል። ይህ የፖለቲካ ቡድን ኢትዮጵያን የማፍረስ ተልዕኮውን ለማሳካት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን መናድ ዋነኛ ትኩረቱ አድርጎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። ቅዱስ ፓትርያርኩን አስገድለው ወይም አገር ጥለው እንዲሰደዱ በማድረግ ሲኖዶሱን ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረት ሲከሽፍ ወደ ሁለተኛው ክፍል ተሸጋግረዋል። ዐብይ አህመድ ዱባይ ሂዶ ሲሳለቅ ይሄንን የወሮበላ ቡድን ጳጳስ ብሎ ለሚሾመው ሳዊሮስ ተልዕኮ ሰጥቶ በጀት እና ጥበቃ መድቦ ነበር። በዘንድሮ ጥምቀት የታየው ኢትዮጵያዊ አንድነትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ከፍ ብሎ መታየት እረፍት የነሳው የኦህዴድ ቡድን በመጨረሻም ዛሬ በኦሮሚያ ከ20 በላይ ጳጳሳት ሾሚያለሁ ብሎ አውጇል። ይህ ነውረኛ ወረራ እና የኑፋቄ መንገድ በቅድስት ቤ/ክ ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም። ከቤተክርስቲያን ቀኖና እና ሥርዓት ውጪ በኃይል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን እንወርራለን ከሆነ ጉዳዩ ወደ ሌላ ያመራል። በራሳቸው መንገድ በነሱ ስርዓት የሚመራ እምነት ፈጥረው ተሿሹመው ከመንግስት ፍቃድ አውጥተው የመረጡትን ሊያመልኩ ይችላሉ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተክርስቲያናትን እና ገዳማትንም ሆነ ስያሜዋን መጠቀም ግን አይችሉም። ይሄንን የሚያስከብር መንግሥት ነኝ የሚል አካል ከሌለ ጉዳዩ የጉልበት ሲሆን ሰማዕትነት የእያንዳንዱን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ በር አንኳኳ ማለት ነው። ————– ጠላት ዲያብሎስ ቢቃወምም ቀስቱን ቢገትር ቢፋለምም የፀናችውን በጌታ ደም የሚረታት ማንም የለም !! የኑፋቄ ጦር ቢሰበቅም የገሀነም ደጆች አይችሏትም

Source: Link to the Post

Leave a Reply