#የዐይን #መነፅር አጠቃቀምየዐይን መነፅር በብዛት እይታን ለማስተካከል ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ለምሳሌ ለንባብ ፣ለፀሀይ እንዲሁም ለመዋቢያነት ጥቅም ላይ የሚውሉ መነፅሮች አሉ፡፡አብዛኛው የማህበ…

#የዐይን #መነፅር አጠቃቀም

የዐይን መነፅር በብዛት እይታን ለማስተካከል ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
ለምሳሌ ለንባብ ፣ለፀሀይ እንዲሁም ለመዋቢያነት ጥቅም ላይ የሚውሉ መነፅሮች አሉ፡፡
አብዛኛው የማህበረሰባችን ክፍልም በተለያየ ምክንያት የአይን መነፅሮችን ይጠቀማል፡፡
ሁሉም ግን በትክክለኛው መንገድ እና የህክምና ባለሙያ ያዘዘለትን የአይን መነፅር ነው የሚጠቀመው ማለት አይቻልም፡፡
የመነፅር አጠቃቀማችን በምን መልኩ መሆን አለበት የሚለውን እንዲነገሩን የዐይን ከሀኪም ከሆኑት ዶ/ር ጉተታ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡
በዋነኛነት የአይን መነፅር በትእዛዝ የሚሰሩ እና ያለትዛዝ የምነጠቀማቸው የአይን መነፅሮች መኖራቸውን ይናገራሉ፡፡

#የትዕዛዝ መነፅር

አንድ ሰው ከርቀት እና ከቅርብ የማየት ችግር ሲገጥመው በስነስርአት ተለክተው በቁጥር የሚቀመጡ እና የሚታዘዙ የመነፅር አይነቶች ነው፡፡
እነዚህን መነጥሮች ከትእዛዝ ውጪ ማድረግ ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል ፡፡

#ከትዕዛዝ ውጪ የሚደረጉ መነፅሮች

እነዚህ በብዛት ለፀሀይ የምንጠቀማቸው መነፅሮች ሲሆኑ ያን ያህል የጎንዮሽ ጉዳት ያላቸው አይደሉም፡፡
መነፅር አጠቃቀም ላይ በተለየ ሁኔታ መጠንቀቀቅ ያለብን ህጻናት ላይ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
ምክንያቱም ልጆች በእድገት ላይ ያሉ ስለሆኑ በየ ስድስት ወሩ መታየት አለባቸው፡፡
በእድገታቸው ወቅትም የመነፅሩ ቁጥር ሊቀያየር ስለሚችል በአይናቸው ልኬት መሰረት እየተቀየረላቸው ማድረግ እንደሚኖርባቸው ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
በየስድስት ወሩ ታይተው ልኬታውን የማያስተካክሉ ከሆነ አይናቸው እስከመንሸዋረር ሊደርስ ይችላልም ብለዋል፡፡

#ያለሃኪም ትእዛዝ እንዲሁም የሌላ ሰው መነፅር መጠቀም #ምን #ያስከትላል?
– ብዥታ
– ማዞር
– ምቾት አለመሰማት
– ኢንፌክሽን መተላለፍ
– እራስ ምታት

#መነፅር ስንጠቀም መደረግ ያለባቸው ነገሮች
– ከሶላር መነፅር ውጪ ተለክቶ ማድረግ
– የመነፅሩን ፍሬም በትክክል መምረጥ
– መነፅሩን ስናስቀምጥ በመስታወቱ በኩል አለማስቀመጥ
– ስናፀዳ ለሱ በተዘጋጀ ነገር ብቻ ማፅዳት
በመጨረሻም እድሜያችን 40 እና ከዛ በላይ እየሆነ ሲመጣ የቅርብ እይታችን እየደከመ ስለሚሄድ አይናችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ላለመፍጠር ሀኪም ቤት ሄዶ የአይን መነፅር እንዲታዘዝንል ማድረግ እንደሚመረጥ ዶ/ር ጉተታ ተናግረዋል ፡፡

በሐመረ ፍሬው

መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply