የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ መግባቱ ታውቋል። ልዑካን ቡድኑ ላንድ ሳምንት ቆይታ አዲስ አበባ የገባው፣ መንግሥት ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መር…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/aZyS5tvU7C_EdgTENrq97-4hvEC-qT9-45X3R8qLCXD9xSXRqfaICVtx-1pKa9L65acP2a-ExgOjI7V0zn4AJIte5QEoiWvGbJi1X3b11McFN1iTy_Kwe6hWPwzCHdduBXRWVKawUvVrdrw4X2lENIU9S8TXgZZbDEajkEkoGACa3Jfi4gP6jiA-Wgd33L-jPQrAWwomG3fTw6BrxKbZetPAnzBzVsoSHrJnned3tBJX5Zh1YDBGtrGDBQ5u74INaJZzDndv0a41OS1Xcs-zl4QpxWnIapigojUPGrmJ1IoXJPFEleaai8ja6UEBvUYnEux-MftyknWFIqzKOH-kug.jpg

የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ መግባቱ ታውቋል።

ልዑካን ቡድኑ ላንድ ሳምንት ቆይታ አዲስ አበባ የገባው፣ መንግሥት ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሩ ማስፈጸሚያ በጠየቀው ብድር ዙሪያ ከፋይናንስ ሚንስቴርና ከብሄራዊ ባንክ ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት ነው።

ኢትዮጵያ ከድርጅቱ በጠየቀችው ብድር ዙሪያ ከስምምነት ላይ ካልደረሰች፣ አበዳሪ አገራት እስከ ቀጣዩ የአውሮፓዊያን ዓመት የሰጧትን የብድር መክፈያ እፎይታ እንደሚሰርዙ ቀደም ሲል አስጠንቅቀዋል።

መንግሥት ከድርጅቱ የጠየቀው ብድር 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነው።

የድርጅቱ ልዑካን ቡድን ካኹን ቀደም ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ በብድር ጥያቄው ዙሪያ የተወያየው ባለፈው ጥቅምት ወር እንደነበር ይታወሳል።

መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply