የዓለም ሙቀት መጨመር 60 በመቶው የአፍሪካን መሬት መጎዳቱን አንድ ጥናት አመላከተ።በአለም ሙቀት መጨመር ሳቢያ በአፍሪካ ከጠቅላላው የመሬት ስፋት 60 በመቶው በመጎዳቱ በከተሞች የሚኖሩ…

የዓለም ሙቀት መጨመር 60 በመቶው የአፍሪካን መሬት መጎዳቱን አንድ ጥናት አመላከተ።

በአለም ሙቀት መጨመር ሳቢያ በአፍሪካ ከጠቅላላው የመሬት ስፋት 60 በመቶው በመጎዳቱ በከተሞች የሚኖሩ ህዝቦችን ኑሮ አስቸጋሪ እንዳደረገው አዲስ ጥናት አመላክቷል።

የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት እ.ኤ.አ. ከ1850 በኃላ ከ 2019 ጀምሮ ያሉት ዓመታት እጅግ ሞቃታማ ጊዜያት መሆናቸውን አውጇል።

በመላው አፍሪካ፣ የተከሰተው ይኸው የሙቀት ሞገድም በአህጉሪቱ ህዝቦች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን የቻይና የሳይንስ ሊቃውንት ቡድን ነው ያስታወቀው።

ሳይንቲስቶቹ እንደሚናገሩት ከህዳር እስከ መጋቢት ባለው ጊዜ ውስጥ በጣም ኃይለኛው የሙቀት ሞገድ በመከሰቱን ሳቢያ በአህጉራችን አፍሪካ ከጠቅላላው የመሬት ስፋት 60 በመቶው መጎዳቱን በጥናቱ አመላክቷል።

በደቡባዊው ንፍቀ ክበብም ላለፉት 24 ቀናት የሙቀት ሞገድ በሦስት ዲግሪ ሴንቲግሬድ የጨመረ ሲሆን፣ በሰሜን ደግሞ ለስምንት ቀናት ያክል የሙቀት መጠኑ በ 1.8 ዲግሪ ሴልሺየስ መጨመሩን የሜትሮዎሎጂ ባለሙያዎች ጥናት አረጋግጧል።

ተመራማሪዎቹ ብዙ ሰዎች በሚኖሩባቸው ከተሞች የሙቀት ክስተቱ እያስከተለ ያለውን ስጋት ገልጸው፣ እነዚህ ቦታዎች በቀጣይ ጊዜያቶች መለነዋሪዎች አስጊ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

የከባቢ አየር ፊዚክስ ተቋም የሆነው የቻይናው የሳይንስ አካዳሚ እንደሚለው በተለይም በምዕራባዊ-ባህር ዳርቻ፣ሰሜን ምስራቅ፣ደቡብ እና ኢኳቶሪያል አፍሪካ አካባቢዎች ስጋቱ እንዳለ ዘ ኢስት አፍሪካ በዘገባው አመላክቷ ል።

የተባበሩት መንግስታት በቅርብ ባወጣው መረጃ በአፍሪካ ቀንድ ድርቅ እየተባባሰ እየመጣ እንደሆነና በቁጥር 13 ሚሊዮን ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል ሲል አስታውቋል።

የውልሰው ገዝሙ
መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply