የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኢትዮጵያ የብር መግዛትን አቅም ካዳከመች የዋጋ ንረቱ እንደሚባባስ አስጠነቀቀ:: የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም ከተዳከመ የዋጋ ንረት እንደሚ…

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኢትዮጵያ የብር መግዛትን አቅም ካዳከመች የዋጋ ንረቱ እንደሚባባስ አስጠነቀቀ::

የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም ከተዳከመ የዋጋ ንረት እንደሚባባስና የነዳጅና ማዳበሪያ ዋጋ እንደሚጨምር ማስጠንቀቁን ከአንድ የድርጅቱ ሰነድ ላይ የተገኘ ሪፖርት አመላክቷል።

መንግሥት የውጭ ኩባንያዎች በአስመጭነትና ላኪነት እና በችርቻሮና ጅምላ ንግድ እንዲሳተፉ የፈቀደው፣ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅትና ከዓለም ባንክ ብድር ለማግኘት ሲል ሊኾን እንደሚችል ሰነዱ አመላክቷል፡፡

ኹለቱ ተቋማት የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም እንደሚፈልጉና፣ የእስካኹኑን የዋጋ ንረት ከአለመረጋጋትና ከዓለማቀፍ የሸቀጦች ዋጋ መጨመር ጋር እንደሚያያይዙት ሰነዱ ያብራራል።

ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ከእያንዳንዳቸው 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት ድርድር ላይ እንደምትገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 03 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply