የዓለም ሬዲዮ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ13ኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል፡፡

ዩኔስኮ በየዓመቱ እ.ኤ.አ የካቲት 5 ቀን የዓለም የሬዲዮ ቀን ሆኖ እንዲከበር መወሰኑን ተከትሉ ዛሬ ለ13ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በኢትዩጲያ የመጀመሪያው የሬዲዮ ስርጭት የጀመረው መስከረም 2 ቀን 1928 ዓ.ም ነበር፡፡

በቀዳማዊ አጼ ኃይለስላሴ “መልካም ፈቃድ” በ1920ዎቹ መጨረሻ ስራ የጀመረው የኢትዮጵያ ሬዲዮ መረጃ በቀላሉ ሊገኝ በማይችልበት በዛን ጊዜ ብቸኛ አማራጭ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ላለፉት 88 አመታትም የብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ ምርጫም ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ሬዲዮን ፈለግ በመከተልም ብዙ የሬዲዮ ጣቢያዎችም ተመስርተዋል። አሁን ላይ ከ60 በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች በአጭር፣መካከለኛ እና ረጅም እንዲሁም በኤፍ.ኤም ሞገዶች የሚያሰራጩ ከ75 በላይ የራዲዮ ጣቢያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኙም መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ሬዲዮ ለሰው ልጆች እድገትና መሻሻል፣ ለችግሮች መፍትሄ ለመሻት፣ ህይወትን ለመታደግ፣የዕለት ተዕለት ኑሮን የተቃና ለማድረግ የሚያስችሉ መረጃዎችን ይሰጣል።

ዓለምን ለማገናኘት፣ ለሙዚቃ ኢንዱስትሪ ልማት፣ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍም ሬዲዮን የሚስተካከለው አልነበረም።ለዚህም ነው የሬዲዮ ፈጠራ ዓለምን የቀየረ ፈጠራ ነው የሚባለው።

የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply