የ‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት” የ2023 አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል፡፡‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት›› በመላው ዓለም ከባድ አደጋዎችንና ፈተናዎችን ተቋቁመው ሰላም፣ ፍትህ፣…

የ‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት” የ2023 አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል፡፡

‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት›› በመላው ዓለም ከባድ አደጋዎችንና ፈተናዎችን ተቋቁመው ሰላም፣ ፍትህ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ የፆታ እኩልነት እና የሴቶች ተጠቃሚነት እንዲከበሩና እንዲሰፍኑ ልዩ ጥንካሬ፣ ጀግንነትና የአመራር ጥበብ ላሳዩ ሴቶች የሚበረከት ሽልማት ነው፡፡

ሽልማቱ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ እስካሁን ድረስም ከ80 ሀገራት የተገኙ ከ180 በላይ ጀግና ሴቶችን እውቅና ሰጥቷል፡፡ በዘንድሮው ሽልማት ከአራት አህጉራት የተገኙ 11 ጀግና ሴቶች እና አንድ የሴቶች ቡድን እውቅና ይሰ’ጣቸዋል፡፡

ለሽልማቱ የሚመረጡት ሴቶች የሚታጩት በየሀገራቱ በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች ሲሆን፤ የመጨረሻዎቹ አሸናፊዎች የሚመረጡት ደግሞ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናትና ባለሙያዎች ነው፡፡

በዚህም መሰረት ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች መዓዛ መሐመድ የ2023 የ‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት (International Women of Courage/IWOC Awards)›› አሸናፊ መሆኗ ታውቋል፡፡

የ2023 የ‹‹ዓለም አቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት (International Women of Courage/IWOC Awards)›› አሸናፊዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ዶ/ር ዘካሪያ ሒክመት (አፍጋኒስታን) – [በቱርክዬ የሚኖሩ]
2. አልባ ሩዳ (አርጀንቲና)

3. ፕ/ር ዳንኤላ ዳርላን – መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ
4. ዶሪስ ሪዮስ – ኮስታ ሪካ

5. መዓዛ መሐመድ – ኢትዮጵያ
6. ሐዲል አብደልአዚዝ – ዮርዳኖስ
7. ባክዛን ቶሬጎዚና – ካዛኪስታን

8. ዳተክ ራስ አዲባ ራድዚ – ማሌዢያ
9. ብ/ጀኔራል ቦሎር ጋንቦልድ – ሞንጎሊያ

10. ቢያንካ ዛሌውስካ – ፖላንድ
11. ዩሊያ ፓይቪስካ – ዩክሬይን

ሴት ኢራናውያን የተቃውሞ ሰልፈኞች [እንደቡድን] ደግሞ ‹‹የማድሊን ኦልብራይት መታሰቢያ የክብር ሽልማት››ን ይቀበላሉ ተብሏል፡፡

የሽልማቱ አሸናፊዎች “International Visitor Leadership Program (IVLP)” በተባለው መርሃ ግብር በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በመዘዋወር ከሴቶች አደረጃጀቶች አመራሮች ጋር እንደሚወያዩና የልምድ ልውውጥም እንደሚያደርጉ ተጠቅሷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply