
በኳታሩ የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ በአል ባይት ስታዲየም ውስጥ በርካታ ወንበሮች ክፍት ሆነው መታየታቸውንና የተከፈላቸው ናቸው የተባሉ “ሐሳዊ” የእግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች የዋና ከተማዋ የዶሃ ጎዳናዎችን ሞልተው መታየታቸው መነጋገሪያ ሆኗል። ቢቢሲ እነዚህ የተከፈላቸው ናቸው የተባሉት ሐሰተኛ ደጋፊዎችን ጉዳይ ለማጣራት ባደረገው ምርመራ ወቅት ኳታር በዓለም ዋንጫ አማካይነት ገጽታዋን የበለጠ ለማጉላት እያደረገችው ያለውን ጥረት ለመረዳት ችሏል።
Source: Link to the Post