
ኳታር እያስተናገደችው ያለውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን የትኛው አገር ይወስዳል? የበርካቶች ጥያቄ ነው። አንዳንዶች ስፖርታዊ ትንታኔን ተከትለው ለመገመት ይሞክራሉ። ሌሎች ደግሞ ‘ጠቋሚ ምልክት’ ይፈልጋሉ። ተስፋቸውን ‘አስማት’ ላይ የጣሉ፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኤአይ) የሚታገዙም አሉ። የኳስ ውጤት መገመት በእርግጥ ቀላል አይደለም። ምክንያታዊ ግምት ቢከተሉም በቁማር ገንዘብ የሚበሉ የበዙትም ለዚያ ይሆናል።
Source: Link to the Post