የዓለም የጤና ድርጅት መሪውን እንዲመረምር ኢትዮጵያ ጠየቀች

በዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ የሥነ-ምግባር ምርመራ እንዲያደርግ ኢትዮጵያ በደብዳቤ ጠየቀች።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለቦርዱ በጻፈው ደብዳቤ “የህወሓት ንቁ አባል እና ደጋፊ ሆነው ቀጥለዋል” ያላቸው ዶ/ር ቴድሮስ፣ “ጽ/ቤታቸውን የፖለቲካ ጥቅማቸውን ለማራመድ እየተጠቀሙበት ነው” ሲል ከሷል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ወደ ትግራይ ክልል መድኃኒቶችን እንዳያስገባ በኢትዮጵያ መንግሥት ተከልክሏል በማለት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግሥትን መውቀሳቸውን ተከትሎ ነው ክሱ የቀረበው፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply