የዓለም ደም ለጋሾች ቀን ሰኔ 7/2016ዓ.ም በአዲስ አበባ በድምቀት ይከበራል ተባለ።የዘንድሮው የደም ለጋሾች ቀን “ለ20 ዓመታት የደም ልገሣችሁ እናመሰግናለን ! ” በሚል መሪ ቃል ሰኔ…

የዓለም ደም ለጋሾች ቀን ሰኔ 7/2016ዓ.ም በአዲስ አበባ በድምቀት ይከበራል ተባለ።

የዘንድሮው የደም ለጋሾች ቀን “ለ20 ዓመታት የደም ልገሣችሁ እናመሰግናለን ! ” በሚል መሪ ቃል ሰኔ 7 2016 አ.ም ይከበራል ሲል የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል።

ዕለቱ የሚታሰበው በጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች ህይወት አድን የሆነውን ደም በበጎ ፍቃደኝነት በመለገስ ለሚያደርጉት ሰብአዊ ተግባር ምስጋና ለማቅረብ እና የደምና ደም ተዋጾኦዎችን አስፈላጊነት ግንዛቤ bማሳደግ መሆኑ ተገልጿል።

በብዙ ሀገሮች በቂና ደህንነቱ የተጠበቀ የደም አቅርቦት ችግር እንዳለ የሚታወቅ ሲሆን የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማትም በቂና ደህንነቱ የተጠበቀ ደም የማቅረብ ተግዳሮቶች እንዳሉባቸው ሰምተናል።

በዋናነት በቂና አስተማማኝ የደም አቅርቦት ሊገኝ የሚችለው ያለማቋረጥ ከመደበኛ የበጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች በሚገኝ የደም ልገሳ መሆኑ ተነግሯል።

የበጎ ፍቃድ ደም ለጋሾች ለሚሰጡት ህይወት አድን አገልግሎት ምስጋና ለማቅረብና ደም ለግሶ ለሌሎች ህይወት መድረስን ለማሳየት እና ቀጣይ አድርገው አንዲሰሩም ለማበረታታት ቀኑ ይከበራል ተብሏል።

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማም በተለያዩ የጎዳና ትርኢቶችና የምስጋና መርሃ ግብር እለቱ በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል።

የዓለም ደም ለጋሾችን ቀንን በማስመልከት ከሰኔ 7/2016 ዓ.ም ጀምሮ አስከ ሰኔ 22/2016ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ተገልጿል።

በ2016 ዓ.ም በ11 ወራት ውስጥ በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ 43 የደም ባንኮችና የደም ማሰባሰቢያ ማዕከላት በድምሩ 3 መቶ 12 ሺ 1 መቶ 76 ዩኒት ደም ማሰባሰብ መቻሉንም ታውቋል።

በሐመረ ፍሬው

ሰኔ 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply