የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ክትባትን አስመልክቶ ፍትሐዊ ክፍፍል እንደሌለ ተገለጸ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በሀብታም እና በድኃ ሀገራት መካከል የኮሮና ቫይረስ ክትባት ክፍፍል ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ አይደለም በማለት ተችቷል፡፡ድርጅቱ በየሀገራቱ የሚደርሰውን የክትባት መጠን ለመታዘብ እንደሞከረ ገልጾ፤ የኮቪድ 19 ክትባት ፍትሐዊነት እንዲኖረው ጥሪ አቅርቧል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ለታዳጊ ሀገሮች የሚቀርብ ኮቫክስ የተሰኘውን ክትባት እያሰራጨ ሲሆን እስካሁን በዕቅዱ ከ38 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን ወደ 100 ሀገራት እንዳዳረሰ ተናግሯል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሓኖም በበኩላቸው ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ከአራቱ ሰዎች አንድ ሰው የኮቪድ 19 ክትባትን  ሲያገኝ፤ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት በአንጻሩ ከ500 ሰው አንድ ሰው ክትባቱን እንደሚያገኝ ገልጸዋል፡፡

በመጪዎቹ ሁለት ወራት ውስጥም ፍትሐዊ ክፍፍል እንዲኖር እንሰራለን ብለዋል፡፡የዓለም ጤና ድርጅት በአንድ ዓመት ውስጥ ሁለት ቢሊዮን የኮቫክስ ክትባትን ለ190 ሀገራት ለማዳረስ እቅድ እንደያዘም አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡-የቢቢሲ ነው፡፡

ቀን 04/08/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

The post የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ክትባትን አስመልክቶ ፍትሐዊ ክፍፍል እንደሌለ ተገለጸ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply