
የ127ኛው የዓድዋ ድል በዓልን በአጼ ምኒልክ አደባባይ ለማክበር የወጡ ነዋሪዎች በፀጥታ ኃይሎች በአስላቃሽ ጭስ ሲበተኑ፣ በጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥም የነበረው ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ሳይጠናቀቅ ተቋረጠ። በዓሉ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ቢሆንም ዋናው የበዓል ሥነ ሥርዓት በተካሄደበት በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም ያልታዩ ሁኔታዎች እንዳጋጠሙ ባለፉት ዓመታት በዓሉን ሲታደሙ የነበሩ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
Source: Link to the Post