You are currently viewing ‹‹የዕዳ ቦንብ!!! የኢትዮጵያ የአገር ውስጥና የውጭ ብድር የዕዳ መጠን!!! ›› (ክፍል አንድ)- ሚሊዮን ዘአማኑኤል

‹‹የዕዳ ቦንብ!!! የኢትዮጵያ የአገር ውስጥና የውጭ ብድር የዕዳ መጠን!!! ›› (ክፍል አንድ)- ሚሊዮን ዘአማኑኤል

አህመድ ሸዴ፣ግርማ ብሩ፣ሶፍያን አህመድ፣ተክለወልድ አጥናፉ፣ዮሐንስ አያሌው፣አብርሃም ተከስተ፣ይናገር ደሴ፣ አቤ ሳኖ፣በቃሉ ዘለቀ፣ባጫ ጊና

የኢትዮጵያ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮችን የዕዳ መጠን ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2011ዓ/ም ዶክተር  ዐብይ አህመድ ለህዝብ ይፋ አድርገው ነበር፡፡ በ2012ዓ/ም ደግሞ ኮቪድ 19 ጣረ-ሞቱን በዓለማችን አህጉራቶች ላይ መረቡን ዘረጋ ዓለም አቀፍ ንግድ ድንበር ዘለል የኤሌክትሮኒክስ ንግድ  ሽያጭ ቢዝነስ ለሸማቾች Business-to-Consumer (B2C) እና የቢዝነስ-ለ-ቢዝነስ/ የንግድ ለንግድ ልውውጥ (Business-to-Business (B2B) የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ  ተሸመደመዱ፡፡ የመጎጎዣና የጭነት አይሮፕላኖች ንግድ በኮቪድ 19 ቫይረስ ድባቅ ተመታ፣ ዓለም አቀፍ የጭነት መርከቦች ንግድ በቫይረሱ ጥቃት ሠጠሙ፣ ድንበር ዘለል አገር አቆራጭ የባቡር መስመሮች ተቆረጡ፣ የዓለም ስታዲየሞች ጩህት በካንቦሎጆ ዝምታ ተዋጡ፣ ትያትር ቤቶች፣ የሙዚቃ ኮንሰርቶች፣  ገቢ ነጠፈ፣ የዓለም ሆቴሎችና ቱሪዝም ገቢ ዶጋ አመድ ሆነ፡፡ ህዝበ አዳምና ሄዋን ስራ ፈት ሆኖ፣ ከቤቱ ተከተተ፡፡ ዲያስፖራው ወደ ሃገር ቤት የሚልከው ገንዘብ ሟሸሸ፣ የዓለም ኢኮኖሚ ውድቀት ሆነ፡፡ በ2012ዓ/ም አገራችን ሰው ሰራሽ ጥፋት፣ ኦነግ ሸኔና  ጽንፈኛ ቄሮ ከተማ አቃጠሉ፣ መንገድ ዘጉ፣ ፋብሪካ አወደሙ፣ ሰው አረዱ፣ እህል አቃጡ፣ መንግሥታዊ መዋቅሮች አጋዩ፣ ብዙ ሽህ ህዝብ ተፈናቀለ፡፡ በሰው ሰራሽ ጥፋት ደግሞ የአንበጣ ወረራ ምክንያት ሰብል ወደመ፣ የጎርፍ አደጋና የውኃ መጥለቅለቅ የእርሻ ምርት ጠፋ፣ የአርብቶ አደሮች የከብት ኃብት ጉዳት ደረሰባቸው፣ የኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ ደዌ ተከተለ፣ ብዙ ሽህ ህዝብ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ  ተመልካችና ጠባቂ ሆነ፡፡ በጥቁር ገበያ የአንድ የአሜሪካ ዶላር 46 ብር ይመነዘራል፡፡ በባንክ ውስጥ በ36 ብር ይመነዘራል፡፡ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲና የባንክ ባለሞሎቹ በውሸት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አድጎል ይሉናል፡፡

 • በንግድ ተቆማትና በሸማቾች የንግድ ልውውጦች Business-to-Consumer (B2C) 412 ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ ሲገመት፣ የግለሰብ ሸማቾች የኤሌክትሮኒክስ ንግድ ድርሻ 11 በመቶ ሽያጭ በመያዝ 9 ትሪሊዮን ዶላር ደርሶል፡፡ የአሜሪካ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ ከጃፓን ሦስት እጥፍ ሲበልጥ፣ ከቻይና አራት እጥፍ እንደሚበልጥ ታውቆል፡፡ በተመሳሳይ የእንግሊዝ የኤሌክትሮኒክስ የሸማቾች ንግድ  ሽያጭ 82 በመቶ ህዝብ ሽያጩን በኤሌክትሮኒክስ በ2017 እኤአ ማከናወናቸው ታውቆል፡፡ ሀገረ ጀርመን በአራተኛ ደረጃ እንዲሁም የኮርያ ሪፓብሊክ አምስተኛ ደረጃ ይዘዋል፡፡
 • የቢዝነስ-ለ-ቢዝነስ/ ንግድ ለንግድ ልውውጥ (Business-to-Business (B2B) የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ9 ትሪሊን ዶላር እንደደረሰ ሲገመት፣ የቢዝነስ-ለ-ቢዝነስ ንግድ ድርሻ 88 በመቶ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ   በመያዝ 9 ትሪሊዮን ዶላር ደርሶል፡፡ ቻይና በቢዝነስ-ለ-ቢዝነስ ንግድ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ አንደኛ ስትሆን አሜሪካ ሁለተኛ፣ እንግሊዝ ሦተኛ ደረጃ ይዘዋል፡በአጠቃላይ ቻይና 440 ሚሊዮን ህዝብ በኢንተርኔት የኤሌክትሮኒክስ   ሽያጭ በማከናወን ከፍተኛውን ደረጃ ይዛለች

የኢትዮጵያ ሃገራችን የኢኮኖሚ እድገት በንግድ ተቆማትና በሸማቾች (B2C) እና የቢዝነስ-ለ-ቢዝነስ (B2B)  የኤሌክትሮኒክስ ንግድ ድርሻ በጣም ኢምንት ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ የፋይናንሻልና የባንክ እድገትም በጣም ኃላቀር ከሆኑት አገራቶች ተርታ ትገኛለች፡፡ የባንክ ባለሞሎቾም በግል ጥቅም የታወሩ፣ በዘር ልክፍት የተዋጡ በመሆናቸው፣ የውሸት የባንክ መረጃ በማቅረብ ሃገሪቱን ከብርሃን ወደ ጨለማ አሸጋገሮት፡፡ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮች የዕዳ መጠን የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አድርጎ ነበር፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግበናል ይለናል፡፡ ለዓለም ኢኮኖሚስቶች የአውሮፓ ህብረት አገራቶችና ዩናይትድ ስቴትስ  ኦፍ አሜሪካ የዕዳ ጫና አሳስቦቸው ነበር፡፡ በ2019እኤአ የኢኮኖሚ ዝግመተኛ ሂደትና የኢኮኖሚስቶች ኢኮኖሚውን ለማሻሻልና ለማሟሟቅ  ያቀረቡት ‹‹የዕዳ ቦንብ›› ቀጣዩን የኢኮኖሚ ችግር ውድቀትና ልምሻ አስከትሎል፡፡ የ2019 እኤአ የዕዳ ጫና ሃምሳ በመቶ ከፍተኛ ነበር ከታላቁ የዓለማችን የንዋይ ውድቀት ጋር ሲወዳደር ስለዚህ የምጣኔ ኃብት ጠበብት በዓለማችን የዕዳ መጠን መጨመር የዕዳ ማፈንገጥ ወይም እዳውን የማይከፍል ሃገራት፣ ቢዝነሶች መጨመር ሳይታለም የተፈታ ነገር ሆኖል የሚሉት፡፡ Rising debt levels in the European Union and the United States had always been a concern for economists. However, in 2019, that concern was heightened during the economic slowdown, and economists began warning of a ‘debt bomb’ occurring during the next economic crisis. Debt in 2019 was 50% higher than that during the height of the Great Financial Crisis. Economists have argued that this increased debt is what led to debt defaults in economies and businesses across the world during the recession. (https://en.wikipedia.org/wiki/COVID-19_recession)

አልማዝን አይቼ፣ አልማዝን ባያት፤ ሦስተኛዋ አልማዝ ብትመጣ ድንገት፣

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከመጋቢት  2010 እስከ መጋቢት 2011ዓ/ም 1ድረስ ባለው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ምን መሻሻል አሳየ፡፡ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮችን የዕዳ መጠን የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አድርጎል፡፡  በዚህም መሠረት ዝርዝር የዕዳ መግለጫ ሰነድ እንደሚያስረዳው፣ 2

አገሪቱ እ.ኤ.አ. እስከ ማርች 2019 ድረስ ያለባት ያልተከፈለ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮች ዕዳ 1.5 ትሪሊን ብር ወይም 52.57 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡

 • የአገሪቱ አጠቃላይ የውጭና የአገር ውስጥ ብድሮች ዕዳ5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፡፡
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮ ቴሌኮም የውጭ ብድር ዕዳ9 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
 • የሌሎቹ የልማት ድርጅቶች የውጭና የአገር ውስጥ አጠቃላይ የብድር ዕዳ 594 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
 • ማዕከላዊ መንግሥትና የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልመለሱት ዕዳ5 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
 • መንግሥት ከንግድ ባንክ የወሰደውን ብድር መመለስ ባለመቻሉ በየዓመቱ እስከ 25 ቢሊዮን ብር ወለድ እየከፈለ ነው
 • ከተጠቀሰው አጠቃላይ የአገሪቱ ዕዳ ውስጥ08 ቢሊዮን ብር ወይም 26.93 ቢሊዮን ዶላር ከተለያዩ የውጭ አበዳሪዎች ተገኝቶ ያልተከፈለ ዕዳ ሲሆን፣
 • የተቀረው5 ቢሊዮን ብር ወይም 25.6 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ከአገር ውስጥ የመንግሥት ባንኮች ማለትም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከብሔራዊ ባንክ ቀጥታ ብድር፣ እንዲሁም ከመንግሥት ሠራተኞችና ከግል ሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና (ጡረታ) ፈንዶች ተወስዶ ያልተከፈለ ዕዳ መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡
 • አገሪቱ ካለባት የውጭ ዕዳ ውስጥ የማዕከላዊ መንግሥት (Centeral Government) ዕዳ7 ቢሊዮን ብር (15.73 ቢሊዮን ዶላር) ሲሆን፣ ቀሪው 319.3 ቢሊዮን ብር (11.17 ቢሊዮን ዶላር) ደግሞ የተለያዩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መንግሥት በገባላቸው የብድር መክፈያ መተማመኛ (Loan Guarantee)፣ ሌሎች ሁለት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ደግሞ ያለ መንግሥት የብድር መክፈያ መተማመኛ፣ በራሳቸው ከውጭ አበዳሪዎች በቀጥታ ተበድረው ያልከፈሉት ዕዳ ነው፡፡
 • የማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ (15.73 ቢሊዮን ዶላር) ወይም 449.7 ቢሊዮን ብር
 • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች (11.17 ቢሊዮን ዶላር) ወይም 319.3 ቢሊዮን ብር
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮ ቴሎኮም ያለ መንግሥት ዋስትና የብድር መክፈያ መተማመኛ ከውጭ የተበደሩት እስከ ማርች 2019 ድረስ ያልከፈሉት ዕዳ 9 ቢሊዮን ዶላር ወይም 111.96 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
 • ሎሎቹ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ማለትም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ገንዘብ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በገቡላቸው የብድር መክፈያ መተማመኛ በመጠቀም ከወሰዱት የውጭ ብድር ውስጥ እስከ ማርች 2019 ድረስ ያልከፈሉት የዕዳ መጠን38 ቢሊዮን ብር (7.27 ቢሊዮን ዶላር) መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡
 • አጠቃላይ የውጭ ብድር ዕዳ እስከ ማርች 2019 ድረስ አገሪቱ ያለባትን ተመሳሳይ ወቅት ድረስ የተመዘገበው አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ ደግሞ5 ቢሊዮን ብር መድረሱን መረጃው ያመለክታል፡፡

አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ በሚመለከት በማዕከላዊ መንግሥትንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን የተወሰደው 730.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን መረጃው ያመለክታል፡፡

በዚህም መሠረት አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ (730.5=343.7+386.8)

 • የማዕከላዊ መንግሥት የአገር ውስጥ ዕዳ7 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣
 • የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የአገር ውስጥ ዕዳ8 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለባቸው መረጃው በዝርዝር ያመለክታል፡፡

ማዕከላዊ መንግሥት ካለበት 343.7 ቢሊዮን ብር የአገር ውስጥ ዕዳ ከፍተኛው መጠን ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ ብድር የተወሰደ፣ እንዲሁም በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ አማካይነት ከሁለቱ የሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና (የጡረታ) ኤጀንሲዎች፣ ማለትም ከመንግሥት ሠራተኞችና ከግል ሠራተኞች የጡረታ ፈንድና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተወስዶ ያልተከፈለ ዕዳ መሆኑን ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል፡፡

በዚህም መሠረት ማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ (343.7= 182+98.2+26.5+37)

 • ከብሔራዊ ባንክ ቀጥታ ብድር፣182 ቢሊዮን ብር
 • በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ አማካይነት ከሁለቱ የጡረታ ፈንዶች፣2 ቢሊዮን ብር
 • ከንግድ ባንክ ብድር 5 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
 • የተቀረው በመንግሥት ቦንድ ሽያጭ አማካይነት ከልማት ባንክና ከሌሎች ምንጮች ተወስዶ 37 ቢሊዮን ብር እስከተገለጸው ወቅት ድረስ ያልተከፈለ የማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ ነው፡፡

ከ730.5 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ ማዕከላዊ መንግሥትን የሚመለከተው ተቀንሶ የሚቀረው 386.8 ቢሊዮን ብር ዕዳ፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድና ከኢትዮ ቴሌኮም ወጭ ያሉትን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሚመለከት እንደሆነ ሰነዱ ያመለክታል፡፡ ነገር ግን የመንግሥት ልማት ድርጅቶቹን የተናጠል ዕዳ ዘርዝሮ አያስቀምጥም፡፡ ከልማት ድርጅቶቹ አጠቃላይ ዕዳ ውስጥ 386 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተወሰደ ሲሆን፣ 800 ሚሊዮን ብር ደግሞ የልማት ባንክ መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡ የመንግሥትን አጠቃላይ የዕዳ መጠንና ዝርዝሮቹን ከያዘው ሰነድ የተለያዩ ከፍተኛ ሥጋቶችን መመልከት የሚቻል ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጤንነት አደጋ ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ነው፡፡ ሰነዱ ከያዛቸው አኃዞች ምልከታ መረዳት የሚቻለው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በቀጥታ፣ እንዲሁም የመንግሥትን የዕዳ ክፍያ መተማመኛ ሰነድ (ቦንድ) በማስያዝ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወሰዱት የረጅም ጊዜ ብድር፣ እንዲሁም ማዕከላዊ መንግሥት ከዚሁ ባንክ ተበድሮ ያልመለሰው የገንዘብ መጠን ድምር እ.ኤ.አ. እስከ ማርች 2019 ባለው ጊዜ ውስጥ 412.5 ቢሊዮን ብር ደርሶል፡፡

ባንኮች የሚሰጡት ብድር ስብጥር (Loan Portfolio) የገንዘብ ተቋማት ጤንነትን ለመለካት የሚያገለግል መሣርያ መሆኑን የሚገልጹት ሪፖርተር ያነጋገራቸው ባለሙያዎች፣ አንድ ባንክ የሚሰጠው ብድር ሰፊ ስብጥር ወይም በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ለሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተበዳሪዎች መሆን እንዳለበት፣ የተበዳሪዎች ስብጥር ሰፊ መሆን በተበዳሪዎች ላይ ሊደርስ የሚችል የንግድ ኪሳራ መጠንን በዚያው ልክ በመቀነስ፣ በባንኩ ብድር ላይ ሊፈጠር የሚችል ተጋላጭነትን ለመከላከል እንደሚያስችል ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ አንፃር ንግድ ባንክ የሰጠው 412.5 ቢሊዮን ብር ለመንግሥትና ለአራት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች መሆኑ የብድር ክምችቱ በአንድ አካባቢ የተከማቸ እንዲሆን በማድረግ፣ ባንኩ ላይ ከፍተኛ ሥጋት እንዲያጠላ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡ ከዚህም በላይ የብድር ስብጥሩን እጅግ ጠባብ ያደረገው ለመንግሥት ልማት ድርጅቶች ከተሰጠው ብድር ውስጥ ከ200 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነው፣ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ብቻ የተሰጠ መሆኑን በማሳያነት ይጠቅሳሉ፡፡

ሪፖርተር ያገኘው አጠቃላይ የአገሪቱ የብድር ሰነድ መረጃ እንደሚሳየው፣ ማዕከላዊ መንግሥትም ሆነ የልማት ድርጅቶቹ ያለባቸውን የንግድ ባንክ ብድር ላለፉት አምስት ዓመታት ከፍለው እንደማያወቁ፣ ነገር ግን ከ17 ቢሊዮን እስከ 25 ቢሊዮን ብር ወለድ ላለፉት ዓመታት በየዓመቱ እየከፈሉ መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡ ባንኩ ለስኳር ፕሮጀክቶች ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ቢሰጥም፣ በርካቶቹ ፕሮጀክቶች በማኔጅመንት ችግር መጠናቀቅ ባለመቻላቸው መንግሥት ባሉበት ሁኔታ በሽያጭ ወደ ግል ሊያዘዋውራቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለእነዚህ ፕሮጀክቶች በብድር የፈሰሰውን 11 ቢሊዮን ብር ያባከነው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ብድሩን መክፈል እንደማይችል በመግለጽ፣ ይህንን ጨምሮ በአጠቃላይ 57 ቢሊዮን ብር እንዲሰረዘለት ሰሞኑን ለመንግሥት ጥያቄ እንደቀረበ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ እንደ ባንክ ያሉ የገንዘብ ተቋማት ውጤታማነት መለኪያ ከሆኑት አንዱ የተቀማጭ ገንዘብ ክምችት መጠን፣ ባንኩ ከሰጠው አጠቃላይ ብድር መጠን ጋር የሚኖረው ምጣኔ ስለመሆኑ የባንክ ሙያ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡ ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስከ ማርች 2019 ድረስ የነበረው አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 496 ቢሊዮን ብር ነበረ ሲሆን፣ ለግሉ ዘርፍ ያበደረውን ሳይጨምር እስከ ተጠቀሰው ወር ድረስ ለማዕከላዊ መንግሥትና ለልማት ድርጅቶች አበድሮ የተመለሰለት የብድር መጠን 412.5 ቢሊዮን ብር መሆኑ የባንኩን ጤንነት ጥያቄ ውስጥ ከቶታል፡፡

ዓርብ ነሐሴ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የበጀት ዓመቱን የሥራ አፈጻጸም ይፋ ያደረገው ባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ አጠቃላይ መጠን በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ 541.2 ቢሊዮን ብር መድረሱን የገለጸ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት የሰጠው አዲስ ብድር 129 ቢሊዮን ብር እንደሆነ አመልክቷል፡፡ ከሰጠው አዲስ የብድር መጠን ውስጥ 106.8 ቢሊዮን ብር መንግሥት የወሰደ ሲሆን፣ ቀሪው 22.2 ቢሊዮን ብር ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ ነው፡፡ ንግድ ባንክ ለመንግሥትና ለልማት ድርጅቶቹ የሰጠው ብድር ከፍተኛ መሆኑና የብድሩ መመለስን በተመለከተ ስለሚነሳው ሥጋት ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበላቸው የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ባጫ ጊና፣ ሥጋቱ ትክክለኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ባንኩ ለመንግሥትም ሆነ ለግሉ ዘርፍ የሰጣቸው ብድሮች እንደሚመለሱ እርግጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ተበዳሪ የሆኑ የልማት ድርጅቶች ብድሩ እንዲሰረዝላቸው ስለጠየቁ ይሰረዛል ወይም ባንኩ ገንዘቡን ያጣል ማለት እንዳልሆነ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ “ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እንዴት እንደምንሄድበት እናውቃለን፡፡ ምክንያቱም ብድሩን ያበደርነው የመንግሥትን ዋስትና ይዘን ነው፤” ብለዋል፡፡ የአገሪቱን አጠቃላይ ብድር የያዘው መረጃ የሚያስገነዝበው ሌላው ጉዳይ፣ መንግሥት በአነስተኛ ወለድ የውጭ ብድር ቢያገኝ እንኳን በርካቶቹ የውጭ ዕዳዎቹ የክፍያ ጊዜ በማለፉ ወይም በመድረሱ ምክንያት የሚያገኘው አዲስ ብድር ተመልሶ ለዕዳ ክፍያ እየዋለ መሆኑን ነው፡፡ ለአብነት ያህል የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አስተዳደር እ.ኤ.አ እስከ ማርች 2019 ድረስ 2.2 ቢሊዮን ዶላር አዲስ ብድር ያገኘ ቢሆንም፣ ለተገኘው አዲስ ብድር የአገልግሎት ክፍያ፣ ክፍያቸው የደረሱ ብድሮች ዋና ብድርና ወለዶች ተከፍሎ ወደ አገር የገባው የአዲሱ ብድር የተጣራ መጠን 700 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሌላ የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሙያ በበኩላቸው፣ መንግሥት ካለበት አጠቃላይ የአገር ውስጥ ብድር ውስጥ 182 ቢሊዮን ብር ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ የተበደረው መሆኑ አሳሰቢ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ መንግሥታት ከብሔራዊ ባንኮቻቸው በቀጥታ መበደር የሚችሉ ቢሆንም፣ የብድር ጣሪያው በሕግ መወሰን እንደሚገባውና ብድሩ በተወሰደበት በዚያው ዓመት መጨረሻ ላይ ሙሉ በሙሉ እንዲከፈል በሕግ ካልተደረገ በስተቀር፣ ውጤቱ ገንዘብ እንደማተም እንደሚቆጠር ይህም ኢኮኖሚው ያላመነጨው ተጨማሪ ገንዘብ በኢኮኖሚው ውስጥ እንዲሽከረከርና የዋጋ ግሽበት እንዲፈጠር የሚያደርግ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

በተጨማሪም መንግሥት ያለ ገደብ ከብሔራዊ ባንክ የሚበደርበት ሥርዓት አለ ማለት፣ ብሔራዊ ባንክ ማክሮ ኢኮኖሚውን ያለ መንግሥት ጣልቃ ገብነት ማስተዳደር አለመቻሉን እንደሚያሳይ ባለሙያው ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ መውሰድ የሚችለው የቀጥታ ብድር ጣሪያ በ2000 ዓ.ም. እንዲነሳ ከተደረገ በኋላ፣ ከብሔራዊ ባንክ ያለ ገደብ እየተበደረ መሆኑ አሁን ለሚስተዋለው የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት የራሱ ድርሻ ማበርከቱን አክለዋል፡፡ አንዳንዶቹ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች እስከ አንገታቸው ድረስ በዕዳ የተዘፈቁና ተጨማሪ ካፒታል እንዲያገኙ ቢደረግ እንኳን መዳን የሚችሉ ባለመሆናቸው፣ በሽያጭ ወደ ግል ተዘዋውረው እንዲተርፉ ማድረግ ለመንግሥት የቀረው ብቸኛው አማራጭ መሆኑን፣ ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተካሄደው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውይይት ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሚሸጡትም ድርጅቶች ከላይ ከፍተኛ ዕዳ ውስጥ የተዘፈቁ መሆናቸው ገልፆል፡፡

 

የተጀመሩት ፕሮጀክቶች ሳይጠናቀቁ ሌላ ፕሮጀክቶች አይጀመሩ!!!

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የፌዴራል ጋርድ ልዩ ጥበቃ ኃይል ይቌቌምለት!!! እንደ ሪፓብሊካን ጋርድ !!!

ምንጭ፡-

{1} ሪፖርተር ጋዜጣ/ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ የብድር ዕዳ 1.5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል/ August 19, 2019/ ዮሐንስ አንበርብር

{2} ከ336 ቢሊየን ብር በላይ የልማት ድርጅቶች ዕዳ አልተመለሰም፣ ዕዳው እንዲሰረዝ አልያም ከበጀት እንዲከፈል ሀሳብ ቀርቧል (ዋዜማ ራዲዮ-) August 18, 2019/Tuesday 28 April, 2020

Leave a Reply