የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 13/2014 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ:: የኢፌዲሪ የህዘብ ተወካዮች ም/ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ማጽደቁ ይታ…

የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 13/2014 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ::

የኢፌዲሪ የህዘብ ተወካዮች ም/ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ማጽደቁ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ከታህሳስ 26/2014 – ጥር 6/2014 ዓ.ም ድረስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

እስካሁን ዕጩ ኮሚሽነሮችን ለመጠቆም ዜጎች ያሳዩት ተነሳሽነትና እያደረጉ ያሉት ተሳትፎ የሚያበረታታ ነው፡፡

ይሁንና ኮሚሽኑ ከሚኖረው ከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነት አንፃር ተጨማሪ ዕጩዎችን ህዝቡ እንዲጠቁም እንዲሁም የአገሪቱን ብዝሃነት ታሳቢ በማድረግና በተለያዩ ምክንያቶች መጠቆም ላልቻሉ ዜጎች ዕድሉን ለመስጠት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 13/2014 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፤

የህዘብ ተወካዮች ም/ቤት፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 05 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply