You are currently viewing የዘመነ ካሴ እስር የአጠቃላይ የአማራ ብሔርተኝነት ፈተና ነፀብራቅ ነው ‼️ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ/ም (አሻራ ሚዲያ)    1. ምንም ማደባበስና መልመጥመጥ…

የዘመነ ካሴ እስር የአጠቃላይ የአማራ ብሔርተኝነት ፈተና ነፀብራቅ ነው ‼️ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ/ም (አሻራ ሚዲያ) 1. ምንም ማደባበስና መልመጥመጥ…

የዘመነ ካሴ እስር የአጠቃላይ የአማራ ብሔርተኝነት ፈተና ነፀብራቅ ነው ‼️ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ/ም (አሻራ ሚዲያ) 1. ምንም ማደባበስና መልመጥመጥ አያስፈልግም። ዘመነ ካሴን አጀንዳ ለማድረግ የተመረጠው ወቅት እጅግ አደገኛ ነው። የአማራ ክልልና ህዝብ በያቅጣጫው በጦርነት ሰቆቃና በስጋት በተወጠረበት በዚህ ቀዉጢ ወቅት ዘመነ ካሴን አታልሎም ይሁን አድፍጦ ማሰር የተጠና እብደት ነው። ሌላ ለመሸፈን ፣ ለማስቀየስ የተፈለገ ጉድ ያለ እንዳለ ይናገራል። 2. የዘመነ እስር አማራን አንገት የማስደፋት ርብርቦሽ አካል ነው። በደጀን ግንባር (home front) የተከፈተብንና አይቶ እንዳላየ ብናልፈውም ያልተላቀቀን ፣ ባለጋራዎቻችን በታላቅ ጥድፊያ ሌት ተቀን የሚሰሩበት አከርካሪ የመስበር ዘመቻ ነው። የሚደረግብን መዋቅራዊ ጥቃት ታሪካችንን ፣ እሴቶቻችንን ፣ ተቋማቶቻችንን ፣ ጀግኖቻችንን ላይ ያነጣጠረ ነው። 3. በተለይ የነፃነታችን ዋስትና የሆነውን ፋኖን ለማንበርከክና ለማጥፋት በተከፈተው ዘመቻ ፣ ከሃዲው መንግሥት ጦርነቱ ሳይቋጭና ፋኖዎቻችን ከቁስላቸውና ከጣመናቸው ሳያገግሙ በአስር ሺዎች እያፈሰና እያሳደደ እረፍት ነስቷቸዋል። እኛም ለስንፍናችንና ለፍርሃታችን ማስተባበያ እየሰጠን የክህደቱ ተባባሪ ሆነናል። ዛሬም ለዘመነም ሆነ ለሌሎች ጀግኖች “ከመሞት መታሰር ይሻላል” እያልን ተንበርካኪነትን እየተቀበልን ነው። 4. አንድ አማራ ሲነካ ሁሉም ይነካል። ዘመነ የአማራ ልጅ የአማራ ታጋይ ነው። ጥፋቱም ልማቱም ሁላችንንም እንደ እናት ልጅ የሚመለከተን ወንድማችን ነው። ጠላቱ ጠላታችን ወዳጁ ወዳጃችን ነው። ያለፍትህ አንዲት የጠጉር ዘለላ እንድትነካበት አንፈቅድም። የዘመነን ጉዳይ የጎጃም ብቻ አድርገህ የምትንገበገብና የማይገናኝ ታሪክ እየቆነፀልክ የምታሳስት ሁሉ ማፈሪያ ነህ። 5. ዘመነን በግል ላትወድደው ፣ በሀሳቡ ላትስማማና ልትቃወመውም ትችላለህ። እንዳባትህ ደመኛ ጉስቁልናውንና ሞቱን የምትመኝና የምታሴር አማራ ከሆንክ ከጠላት ለይቼ አላይህም። በተለይ የአማራ ብሔርተኛ ነኝ ከምትል ከሃዲ ጋር ህብረት አይኖረኝም። ለነገሩ ፋኖን ፋኖ ሲጠላና ለጠላት አሳልፎ ሲሰጥ አላየንም። ፋኖን የሚከፋፍል ፣ በፋኖ ስም የሚነግድና ለጠላት የሚሸጠው በየመንደሩ የሚያውደለድለውና በአማራ ስም የሚነግደው የሚዲያ አርበኛ ፣ ተከፋይ አክቲቪስትና ምንደኛ ፖለቲከኛ ነው። 6. ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ነው። ጥርስ አልባ ትግል ሰላሳ ዓመት ሙሉ ለአልፎ ሂያጅ መዛበቻነትና ለውርደት ዳርጎናል። እንደ ህዝብ መናደድ ፣ መቆጨትና መቆጣት አለብን። በማንኛውም መንገድ መብታችንን ለማስከበር ፣ መሪዎቻችንን ፣ ጀግኖቻችንንና ተቋማቶቻችንን ከአደጋ ለመጠበቅ ቁርጠኛ መሆን አለብን። በምድር አንቀጥቅጥ ተቃውሞ መንግሥት ለማስገደድ ፣ የጭቆናና የጥቃት መዋቅሮችን ለማፍረስ ፣ መካከላችን ተወሽቆ ጀግኖቻችንን የሚያስበላውን ባንዳ ፣ ምንደኛና ጎጠኛ አደብ ማስገዛት ካልጀመርን ለቅሷችን ይቀጥላል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply