
በዩክሬን እየተካሄደ ባለው ጦርነት የሩሲያ ሠራዊትን ግስጋሴ በመግታት በኩል የዩክሬን ኃይሎች የታጠቋቸው ቱርክ ሰራሾቹ ባይራክታር ቲቢ2 ድሮኖች ከፍተኛ ድርሻ አላቸው። ዝነኛው ቱርክ ሰራሹ ባይራክታር ቲቢ2 የተባለው ድሮን የጦርነትን ገጽታ በመቀየር በኩል ጉልህ ሚና እንዳለው ባለሙያዎች ይናገራሉ። ይህ ድሮን ሁለት ሚሊዮን ዶላር የሚያስወጣ ሲሆን መጠኑም አነስ ያለ አውሮፕናን የሚያክል ሆኖ፣ በጨረር የሚመራ በረት ለበስ የሆኑ ነገሮችን የሚያወድም ሚሳኤል ይታጠቃል።
Source: Link to the Post