የዘማች ቤተሰቦችን አዝመራ በመሰብሰብ ረገድ የመንግስት ሰራተኞች ተሳትፎ እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በ…

የዘማች ቤተሰቦችን አዝመራ በመሰብሰብ ረገድ የመንግስት ሰራተኞች ተሳትፎ እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ጎጃም ዞን በደባይ ጥላት ግን ወረዳ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በዘመቻ እየሰበሰቡ ነው፡፡ በደባ ጥላት ግን ወረዳ ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሲሰበስቡ ያገኘናቸው በአንገች ቀበሌ የዘማች ቤተሰቦች አዝመራ ስብሰባ አስተባባሪ አቶ ጎጃም ይገዛል “ከቀበሌያችን ወደ ግንባር የዘመቱ ግለሰቦችን አዝመራ ከሌላው ነዋሪ አዝመራ ቅድሚያ ሰጥተን እየሰበሰብን ነው” ብለዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከቀበሌያችን የዘመቱትን ግለሰቦች የጤፍ አዝመራ አጭደን እያጠቃለልን ሲሆን ወቅተን ከቤት እስከማስገባት ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላልን ብለው ህዝቡም በአዝመራ ሰብሰባ ብቻ ሳይሆን የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ከማውጣት በተጨማሪ ወደ ግንባር ለመዝመት ቁርጠኝነቱን በወኔ እየገለጸ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቶ አወቀ አያ በበኩላቸው የህዋሓት ጁንታ የደነቀውን የህልውና አደጋ ለመመከት በሚደረገው ዘመቻ በየዘርፉ ሁሉም አካል እየተሳተፈ ነው ብለዋል፡፡ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ አመራሮችንና የመንግስት ሰራተኞች ሰራዊት ወደ ግንባር ከመላክ ጀምሮ ሎጀስቲክ በመሰበሰብና የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ እያደረጉት ያለው ተግባር በጣም ጠንካራ ነው ተብሏል፡፡ የሌላው አካባቢ ማህበረሰብም በዚህ ወኔ የህልውና ዘመቻውን በየዘርፉ መቀላቀል አለበት ብለዋል፡፡ የአንገች ቀበሌ ግብርና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ቻሌ አንዷለም እንደገለጹት የቀበሌ አመራሩንና ነዋሪውን ማህበረሰብ በማስተባበር የዘማች ቤተሰቦችን አዝመራ እየሰብሰብን ነው ብለዋል፡፡ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ሽመልስ አሳቡ እንደተናገሩት የዘማች ቤተሰቦች አዝመራ ከሌሎች ግለሰቦች አዝመራ ቀድሞ መሰብሰብ አለበት። አቶ ሽመልስ በመጨረሻም የመንግስት ሰራኞች በራሳቸው ተነሳሽነት የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ እያደረጉት ላለው ትልቅ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ስለማቅረባቸው የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ዘገባ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply