‹የዘንድሮውን በዓል የምናከብረው እጅ ከፈንጅ ከያዝነው መንግሥታዊው የታሪክ ሌባ ቡድን ጋር ተፋጠን ነው።› የአማራ ሚዲያ ማእከል  የካቲት 23 2013 ዓ/ም ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓ…

‹የዘንድሮውን በዓል የምናከብረው እጅ ከፈንጅ ከያዝነው መንግሥታዊው የታሪክ ሌባ ቡድን ጋር ተፋጠን ነው።› የአማራ ሚዲያ ማእከል የካቲት 23 2013 ዓ/ም ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓ…

‹የዘንድሮውን በዓል የምናከብረው እጅ ከፈንጅ ከያዝነው መንግሥታዊው የታሪክ ሌባ ቡድን ጋር ተፋጠን ነው።› የአማራ ሚዲያ ማእከል የካቲት 23 2013 ዓ/ም ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በዓለም ዙሪያ ለሚገኝ ጥቁር ሕዝብና በዓሉን ለሚያከብሩ የሰው ልጆች ሁሉ መልካም የአድዋ ድል በዓል እንዲሆን ይመኛል። የዘንድሮውን በዓል የምናከብረው እጅ ከፈንጅ ከያዝነው መንግሥታዊው የታሪክ ሌባ ቡድን ጋር ተፋጠን ነው። ይህ ቡድን ንጉሰ ነገስት እምዬ ምኒልክን እና ብርሐን ዘ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱን ከአድዋ ታሪክ ለመሰረዝ እየተፍጨረጨረ ይገኛል። በምትኩ መንግሥታዊ ሥልጣኑን ተጠቅሞ የራሱን ልብ ወለድ ከመፃፍ አላወተተም። ስለዚህ ባልደራስ የታሪክ ዝርፊያውን የሚያስቆም ታሪክ አድን ግብረ ሃይል እንዲቋቋም ለሕዝብ በተለይም ለከፍተኛ የትምህርትና የምርምር ተቋማት፣ ለምሁራን፣ ለሲቪክ ድርጅቶች፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎችና ለታሪክ ባለሙያዎች ሀገራዊ ጥሪውን ያቀርባል። ሕዝባችን የታሪክ ዝርፊያውን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃኑ እንዳሳየው ሁሉ አምርሮ ሊቃወመው ይገባል። ጀግኖች አርበኞቻችን ይዘውት የዘመቱትን ንፁህ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቃላማ እና ድሉን ብሎም ታሪኩን የሚወክሉ አልባሳትን በመልበስ በአድዋ ዘማቹ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እና በእምዬ ምኒልክ ሀውልት ዙሪያ በዓሉን እንዲያከብር ሀገራዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ሰንደቃላማ እና ከላይ የተጠቀሱትን አልባሳት ማግኘት የማትችሉ ብሎም በተጠቀሰው ቦታ መገኘት የማትችሉ በያላችሁበት በቻላችሁት መጠን እና ሁኔታ በዓሉን ታከብሩ ዘንድ ባልደራስ ያሳስባል። አድዋን በማስመልከት በኦሕዴድ/ብልፅግና የተጀመሩ ማናቸውም ፕሮጀክቶች የታሪክ ዝርፊያው አካል እንደሆኑ እናምናለን። በመሆኑም ጅምሮቹ እንዲቋረጡ ባልደራስ ይጠይቃል። በተለይም ከአመት በፊት በአቶ ታከለ ኡማ መሪነት በአዲስ አበባ የተጀመረው የአድዋ ሙዚየም ግንባታ ፕሮጀክት አሁኑኑ ሊቋረጥ ይገባል። ምክንያቱም አላማው የታሪክ ነጠቃ እና ዳግማዊ ምኒልክን ከአድዋ የድል ታሪክ ማሸሽ ነው። ይህ ደግሞ ከሀዲነት ነው። ለዚህም ነው የሙዚየሙን ግንባታ ባልደራስ ገና ከጅምሩ ከአንድ አመት በፊት የተቃወመው። ይህ ትውልድ መንግሥታዊ ክህደትን በመቃወም ታሪክ እንዲያስቀጥል ፓርቲያችን ሀገራዊ ጥሪውን ያቀርባል። የግንባታው መሰረት ገና መሬቱን ሳይለቅ የዘንድሮው የድል በዓል ማክበሪያ አርማ ተብሎ እምዬ ምኒልክን ያገለለ አዲስ የአድዋ መገለጫ ምልክት ወጥቷል። የሙዚየሙን ግንባታ የምንቃወመው በሚከተሉት አበይት ምክንያቶች ነው፦ ፩. ከመርህ አንፃር እንዲህ አይነት ሙዚየም መገንባት ያለበት በዴሞክራሲያዊ ሂደት በሕዝብ በተመረጠ መስተዳድር በመሆኑ ነው። ፪. ገንቢው ቡድንና ማህበራዊ መሰረቱ የአድዋ ድልን በበጎ የሚረዱ አለመሆናቸው፤ ከተማውን የተቆጣጠረውና ሙዚየሙን የሚገነባው ሃይል የአድዋ ድልንም ሆነ ምኒልክን በመጥፎ የሚረዳ ነው። ድሉን ራሱን መጥፎ አድርጎ የሚቆጥር ነው። የምኒልክን ሃውልት ይፍረስ የሚል የፖለቲካ ማሕበራዊ መሰረት ያለው ነው። ያውም በሰላማዊ መንገድ አይደለም፤ በሃይል አፈርሳለሁ የሚል ነው። ስለዚህ ድርጊቱ ለከሳሽ የዳኝነት ሥልጣን እንደመስጠት ይቆጠራል። ፫. የታሪክ ሽሚያ ነው። እስከ ዛሬ የአድዋ ድል በአዲስ አበባ የሚከበረው ምኒልክ ሀውልት ሥር ነው። ከዚህ በኋላ ማክበሪያ ማዕከሉ ይህ እንዳይሆን ታስቦ ነው የፕሮጀክቱ ግንባታ የተጀመረው። ስትራቴጂያዊ ግቡ ይህ ነው። ኦሕዴድ በሁለት በኩል ማለትም በአዲስ አበባ መስተዳድር እና በኦሮሚያ መስተዳድር በኩል ተሰልፎ በዓሉን ወደ መስቀል አደባባይ እየወሰደው ይገኛል። ፬. ታሪኩን ለማንሻፈፍ ነው። የፈጠራ ታሪኮችን ለመጨመር ነው። ፭. የሙዚየሙ ግንባታ በራሱ የከተማው ኗሪ አንገብጋቢ ጥያቄ አይደለም። ታሪኩን ለማጥፋት ያለሙ ፖለቲከኞች ተነሳሽነት ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንን በመረዳት በሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞ ታሪኩን እንዲያስቀጥል ባልራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሀገራዊ ጥሪውን ያቀርባል። ድል ለዴሞክራሲ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply