የዘንድሮ (2012ዓ.ም.) የበጎ ሰው ልዩ ሽልማት አሸናፊዎች ስምንት ናቸው
–
1) አቶ ካሊድ ናስር
ባለፉት አምስት ወራት በኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ምክንያት የገዛ መኖሪያ ግቢያቸውን ሳይቀር በመስጠት፣ መጠለያ የሌላቸውን በመደገፍ የበጎ አድራጎት ሥራ የሠሩ፤
–
2) አቶ ኪሮስ አስፋው ፡
ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ያለማቋረጥ መቶ ጊዜ የሕዳሴ ግድብ ቦንድ የገዙ፤
–
3) ቢኒያም ከበደ ፡
የንባብ ለሕይወት መሥራች አዘጋጆች አንዱ እንዲሁም የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቭዥን መሥራች፤
–
4) መሀመድ አል አሩሲ
የህዳሴው ግድብ ተሟጋች ፡ በተለይም በአረብኛ ቋንቋ ከግብፆች ጋር በሚዲያ እየተናነቀ የሚገኝ ወጣት
–
5) ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ
አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ መምህሩ እንዲሁም በውሃ ዲፕሎማሲው ዘርፍ ከህዳሴ ግድቡ ግንባታ ጀምሮ አስተዋፅኦ እያበረከቱ የሚገኙት ፣ ብሎም መፅሃፍ የፃፉት ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ የ8 ኛው በጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።
–
6) ኢትዮ ቴሌኮም
በዓመቱ ውስጥ በተለይ ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ በሰራቸው የበጎ አድራጎት ሥራዎቹ የ2012 የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ድርጅቱን በመወከል የተገኙት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
–
7) የሕክምና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች
የኮሮና ወረርሽኝ በሀገራችን ከተሰረተ ጀምሮ ራሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው የዜጎች ደኅንነት ለመጠበቅ ከፊት የተሰለፉ የጤና ባለሞያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የ2012 የዓመቱ የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በመድረኩ የጤና ባለሞያዎችንና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በመወከል ተገኝተዋል፡፡
–
8) የህዳሴው
Source: Link to the Post