“የዘገዬ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል” የሚለውን መርህ እከተላለሁ የሚለው የፌደራሉ ከፍተኛ ቤት የእነ መ/ር ደህናሁን ቤዛን መዝገብ ዳኛ አልተሟላም በሚል ለ4ተኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።…

“የዘገዬ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል” የሚለውን መርህ እከተላለሁ የሚለው የፌደራሉ ከፍተኛ ቤት የእነ መ/ር ደህናሁን ቤዛን መዝገብ ዳኛ አልተሟላም በሚል ለ4ተኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ክልል ከጎንደር፣ ከደብረ ታቦር፣ ከፍኖተ ሰላም፣ከደብረ ማርቆስ፣ ከደሴ፣ ከደብረ ብርሃን እና ከባ/ዳር በክልሉ መንግስት ከተያዙት በርካታ ወጣቶች መካከል 8 የሚሆኑትን በሌሊት አፍነው ወደ አዲስ አበባ ፌደራል ፖሊስ እንዲመጡ ያደረጓቸው ወጣቶች በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት በተደጋጋሚ እየተመላለሱ ይገኛሉ። በተለይም ከሰኞ ህዳር 12/2015 ጀምሮ፣ማክሰኞ፣ረቡዕ በተከታታይ የተመላለሱት እነዚህ ወጣቶች ዳኛ አልተሟላም በሚል ለ4ተኛ ጊዜ ለነገ ህዳር 15/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በችሎት ተገኝቶ እንደተከታተለው እና ጠበቃ ሀብተ ማርያምን እንዳነጋገረው እነ አርበኛ ዘመነ ካሴ ይፈቱ በሚል በበራሪ ወረቀት እና በማህበራዊ ሚዲያ ቅስቀሳ አድርጋችኋል በሚል በሽብር ፈጠራ ተጠርጥረዋል በሚል በአባ ሳሙኤል እስር ቤት የሚገኙ 7 እና ሜክሲኮ በሚገኘው በፌደራል ፖሊስ እስር ቤት ያለው ጋሻው ሲሳይ ከዳኛ አለመሟላት ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ እየተመላለሱ ነው። ከአማራ ክልል እንዲመጡ የተደረጉ እነዚህ 8ቱ ወጣቶች:_ 1) ደህናሁን ቤዛ፣ 2)አንማው ሙላት፣ 3) ብሩክ አያልነህ፣ 4) አምሳያው አዳሙ፣ 5) ዳንኤል ዮሐንስ፣ 6) ታሪኩ በላይ፣ 7) ጥላሁን ደምሴ እና 😎 ጋሻው ሲሳይ ሲሆኑ ጉዳያቸው በሁለት መዝገብ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት እየታዬ የቆዬ ቢሆንም ከእለተ ማክሰኞ ህዳር 13/2015 ጀምሮ መዝገባቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በአንድ ላይ እየተጠሩ ጎን ለጎን እየቀረቡ ይገኛሉ። ህዳር 12 እና 13/2015 ቀርበው ዳኛ አልተሟላም በሚል ህዳር 14/2015 እንዲቀርቡ መቀጠራቸውን ተከትሎ የተገኙ ቢሆንም አሁንም ዳኛ አልተሟላም በመባሉ ለ4ተኛ ጊዜ ተለዋጭሸቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ከአሁን ቀደም በነበረው ችሎትም ከሶስቱ ዳኞች አንዷ ጉዳዩ ሊያስከስሳቸው አይገባም በሚል የልዩነት አቋም የያዙ መሆናቸውን ተከትሎ እየተሰየሙ አይደለም። ከጥቅምት 23 እና 24/2015 ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙት ወጣቶችም ከአሁን ቀደም በህወሓት መራሹ ስርዓት በተደጋጋሚ ለግፍ እስር እና እንግልት ተዳርገው እንደነበር በማውሳት አሁንም ያ ግፍ እና መጉላላት እየተደገመ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለአሚማ ሰጥተዋል። “የዘገዬ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል” የሚል መርህን እከተላለሁ የሚለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ አልተሟላም በሚል ለ4ተኛ ጊዜ ቀጠሮ መስጠቱን ለመመልከት ተችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply