የዜጎቻችንን ክብር ዝቅ ያደረገና ሚሊዮን እናቶችን መካን ያደረገዉን ችግር በቅንጅት ሠርቶ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን መንገድ መዝጋት ያስፈልጋል ሲሉ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ…

የዜጎቻችንን ክብር ዝቅ ያደረገና ሚሊዮን እናቶችን መካን ያደረገዉን ችግር በቅንጅት ሠርቶ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን መንገድ መዝጋት ያስፈልጋል ሲሉ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ…

የዜጎቻችንን ክብር ዝቅ ያደረገና ሚሊዮን እናቶችን መካን ያደረገዉን ችግር በቅንጅት ሠርቶ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን መንገድ መዝጋት ያስፈልጋል ሲሉ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ አሻራ ሚዲያ የካቲት 24/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር የሠራተኛና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰው የመነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻጋር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ብሔራዊ የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነው። በመድረኩ ላይ የዓለም የሥራ ድርጅች በኢትዮጵያ ዳይሬክተር አሌክሲዮ ሙሲንዶ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ውስብስብና ሰፊ ሥራን የሚጠይቅ ነው ብለዋል። ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት በልዩ ትኩረት የሚሠራበት ዘርፍ መሆኑንም አንስተዋል። … በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች በዚህ ሂደት ከፍተኛ ተጠቂዎች እየሆኑ እንደሆነም ተናግረዋል። ቀድሞ የመከላከል ሥራ መሥራት ቁልፉ መፍትሄ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የሲቪክ ማህበራት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና እያንዳንዱ ዜጋ ኀላፊነቱን መወጣት እንዳለበትም መክረዋል። የኢፌዴሪ ሠራተኛ ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋየ ህገ ወጥ አዘዋወሪዎች ከሞራልና ሕግ በወጣ ህሊናቸው ዜጎቻችን ወጥተው እንዲቀሩ አድርገዋል ብለዋል። በየበረሃው፣ በየባህሩና ኮንቴነሩ አስከሬን እንኳን በክብር በማያርፍበት ሁኔታ አስከፊ ሰቆቃዎችን እየታዩ እንደሆነም ተናግረዋል። ሰዓአዊ ፍጡር የማይሸከመው ዘግናኝ ድርጊት በህገወጥ ዝውውሩ በህፃናት፣ ሴቶችና ወጣቶች ላይ እየደረሰ እንደሆነም ገልጸዋል። የሚወሰደው ርምጃም በመከላከል ሥራው ስላልታገዘ ውጤታማ እንዳልሆነ ሚኒስትሯ አንስተዋል። የዜጎቻችንን ክብር ዝቅ ያደረገና ሚሊዮን እናቶችን መካን ያደረገዉን ችግር በቅንጅት ሠርቶ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን መንገድ መዝጋት ያስፈልጋል” ብለዋል። መንግሥት ሀገር ውስጥ መሥራት የሚቻልባቸውን እድሎች መፍጠርና ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል። የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን “በህገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ድንበር የማሻገር ወንጀል ዓለምን እየተፈታተነ ነው፤ በሀገራችን ደግሞ እጅግ የከፋና ዜጎችን በተስፋ ወደማያውቁት ሀገር ህልም በመውሰድ ለሰቆቃ እየዳረገ ነው” ብለዋል። የነፃነት ምልክት የሆን ሕዝቦች በህገወጥ ዝውውሩ የማይመጥነን ድርጊት እያስተናገድን ነው” ያሉት አቶ ደመቀ መኮንን በየሀገራቱ ኢትዮጵያዊያን ከሚደርስባቸው ህይወት ማለፍ በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያለው ዜጋ በእስር ቤት ይገኛል ብለዋል። ከ34ሺህ በላይ ዜጎች በሳውዲ እስር ቤት ብቻ ይገኛሉ፤ አብዛኞቹ በህገወጥ መንገድ የሄዱ ናቸው፤ በየሳምንቱ ቢያንስ 1 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ እየተሞከረ ቢሆንም በሌላ መንገድ ደግሞ በህገወጥ የሚሻገር በርካታ ዜጋ አሁንም መኖሩን ገልጸዋል፡፡ ድንበር ተሻግሮ መሥራትን በሕጋዊ መንገድ ማሳካት ይቻላል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ህገ ወጥ መንገድን ከምንጩ ማድረቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply