“የዜጎችን መሰረታዊ መብት ማፈንና ማገድ ሰፊው ህዝብ ሌሎች የመብት ማስከበሪያ በሮችን እንዲያንኩዋኩዋ መግፋት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል!” ሲል ባልደራስ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

“የዜጎችን መሰረታዊ መብት ማፈንና ማገድ ሰፊው ህዝብ ሌሎች የመብት ማስከበሪያ በሮችን እንዲያንኩዋኩዋ መግፋት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል!” ሲል ባልደራስ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

“የዜጎችን መሰረታዊ መብት ማፈንና ማገድ ሰፊው ህዝብ ሌሎች የመብት ማስከበሪያ በሮችን እንዲያንኩዋኩዋ መግፋት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል!” ሲል ባልደራስ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በአማራ ወገኖቻችን ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ ግድያ መፈናቀል ስደትና ጥላቻን መንግስት ለማስቆም አለመቻሉ አለመፈለጉ ሀገር እንድትፈርስ በአሳዛኝ ሁኔታ ተግባራዊ ፍቃድ መስጠት ሆኖ አግኝተነዋል ብሏል ባልደራስ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክቱ። ይህንን የውድ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ሞት ሀዘንና ስቃይ አስመልክቶ አደባባይ ወጥተን ሀዘናችንን እንገልጻለን ድምጻችንን ለአለም እናሰማለን ያሉ ዜጎችን ከሰላማዊ ሰልፍ መግታቱ የአምባገነንነት ቁንጮ መሆኑ መታወቅ አለበትም ብሏል። በተጨማሪም የዜጎችን መሰረታዊ መብት ማፈንና ማገድ ሰፊው ህዝብ ሌሎች የመብት ማስከበሪያ በሮችን እንዲያንኩዋኩ መግፋት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ሲልም አክሏል። በመጨረሻም በማንነታቸው ምክንያት በግፍ ህይወታቸውን ላጡ ውድ ወገኖቻችን ኢትዮጵያውያን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ጥልቅ ሃዘኑን ይገልጻል፤ለወላጅ ለዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply