
በአሁኑ ጊዜ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ ቢያንስ በ13 አገራት ከ90 በላይ ሰዎች ላይ መከሰቱ የዓለም ጤና ድርጅት አረጋግጧል። በሽታው በስፋት የታየው በአሜሪካ እና በአውሮፓ አገራት ውስጥ ነው። በንክኪ የሚተላለፈው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከኮቪድ-19 ጋር ሲነጻጸር የመዛመት ፍጥነቱ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ እንደ ዩናይትድ ኪንግድም ያሉ አገራት “ችላ የምንለው አይደለም” ብለው በልዩ ትኩረት እየሰሩ ነው።
Source: Link to the Post