You are currently viewing የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናው በትክክል አልታረመም ሲል የሰሜን ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ቅሬታ አቀረበ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 10 ቀን 2014 ዓ.ም         አዲስ አበ…

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናው በትክክል አልታረመም ሲል የሰሜን ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ቅሬታ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበ…

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናው በትክክል አልታረመም ሲል የሰሜን ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ቅሬታ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ጎንደር ዞን ከተፈተኑት 3682 ተማሪዎች ውስጥ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው የመግቢያ ነጥብ ያመጡት 386 ናቸዉ። ይህም የእቅዱን 10.8 % ሲሆን ትምህርት ሚኒሲቴርን ያህል ግዙፍ ተቋም በቅሬታ የተስተካከለ ውጤት የእርማት ስህተት ማሳያ መኖሩን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አረጋግጧል። አስረኛ ክፍል ሁሉንም የትምህርት ዓይነት “A” ያመጡትና 12ኛ ክፍልም በደረጃ የተማሩ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተናውን ውጤት አለማምጣታቸው የፈተና እርማት ስህተት መኖሩን ያሳያል ያሉት የዞኑ ትምህርት መምሪያ ጏላፊ አቶ ክቡር አሰፋ ናቸው። መውደቅና ማለፍ ያለና የነበረ ቢኾንም በዞኑ ዳባት ወረዳ ቁጥር አንድ መሰናዶ ትምህርት ቤት አንድ ተማሪ 170 ተብሎ የተሰራለት ውጤት ባቀረበው ቅሬታ መሠረት ሲፈተሽ 541 ሆኖ መስተካከሉ የእርማት ስህተቱ ማሳያ ነው ብለዋል። የ2013ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከተወሰዱ 3682 ተማሪዎች ውስጥ 386 ብቻ መኾኑ ውጤቱ በጣም ዝቅተኛና አሳሳቢ እንደኾነም ገልጸዋል። የትምህርት ሚኒስቴር ያስቀመጠው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ዞኑ የቆየበትን ችግር እና ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ ውሳኔ በመሆኑ አካባቢውን ለባሰ ችግር ውስጥ እንዲገባ ያደረገ ነው፤ ስለዚህ የትምህርት ሚኒስትሩ የወሰነውን የከፍተኛ ትምህርት ማለፊያ ነጥብና የተማሪዎችን ውጤት በደንብ መርምሮ ማስተካከያ እንዲያደርግ ሲሉ ጠይቀዋል። ሚኒስቴሩ ቅሬታ አቅራቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ ውጤታቸውን ቢያሻሽል የሚል አስተያየትም ሰጥተዋል። የደባርቅ ከፍተኛ ሁለተኛ መሠናዶ ትምህርት ቤት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ማርቆስ ፍኖተ ሰላም የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መውሰዱን ተናግሯል። በወቅቱ ዝቅተኛ ውጤት ካመጡት ተማሪዎች አንዱ ነው። ከአንደኛ እስከ አስረኛ ክፍል ድረስ ደረጃ ይዞ ከክፍል ክፍል ሲዘዋወር እንደነበር ገልጿል። ነገር ግን ለውጤቱ ማሽቆልቆል ምክንያት ነው ያለው በሌሎች ክልሎች ፈተናው ተሰርቆ ተሠራ የሚለው የስነ ልቡና ጫና ፈተናውን እንዳይሠራ አድርጎታል። በእርማቱም ችግር ያለበት በመኾኑ የሚቻል ከኾነ እንደገና ቢታይልን የሚል አስተያየት ሰጥቷል ሌላኛው የማኅበራዊ ሳይንስ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናውን ካለፉት የ12ኛ ክፍል መካከል አንዱ ተማሪ አብዩ እሸቴ ነው። የዚህ ዓመት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ዝቅተኛ መኾን ምክንያት ይኾናሉ ያላቸውን ጉዳዮች ዘርዝሯል። በአንዳንድ አካባቢዎች በፈታኝ መምህራን ኩረጃ መደገፉ የፈተና ጥያቄዎች ቀድመው እየተሠረቁ መሠራጨታቸው፣ ከፈተና በፊት ቀድመው ወጥተው ዝግጅት የተደረገባቸው የሚመስል ነገር መኖሩን ጠቁሟል፤ የ11ኛ ክፍል በኮሮና ምክንያት በመዘለሉና ትምህርቱ አለመከለሱንም እንደችግር አንስቷል። የትምህርት ቤቱ የ12ኛ ክፍል የሒሳብ መምህር ኢዮብ ተቀባ ተማሪዎች ፈተናውን ያልሰሩበት ምክንያት ያሉት ሰሜኑ ክፍል የጦርነት ቀጠናና በህልውና አደጋ ላይ ስለነበር ተደራጅተው ለመከላከል የህልውና ዘመቻ ጥሪውን በመቀላቀላቸውና በስነ ልቦና ጫና ውስጥ መቆየታቸው እንደኾነም ገልጸዋል። በመምህራን ዘንድ የሚመሠከርላቸው በተሻለ የሚሠሩ ተማሪዎችም በእርማት ስህተት ውጤታቸው ዝቅተኛ ነው ብለዋል። በራሳቸው የሚተማመኑ ተማሪዎች ውጤት ላይ የእርማት ችግር በመኖሩ መንግሥት/ የትምህርት ሚኒስቴሩ/ እንደገና ሊፈትሸው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። በአስተማሪዎች በኩል በቂ ዝግጅት እንዲኖራቸው ጥረት ለማድረግ ተችሏል ብለዋል። በቀጣይ ከዚህ ቁጭት በመነሳት ተማሪዎችን ለማብቃት እየሠሩ መኾኑንም ጠቅሰዋል። የሰሜን ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply