የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ ያለፉት ሦስት በመቶ ብቻ ናቸው

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-44c8-08dbc909b586_w800_h450.jpg

በኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ከወሰዱት የሁለተኛ ደርጃ ተማሪዎች መካከል ያለፉት ሦስት በመቶ ብቻ መሆናቸውን የሀገሪቱ የትምህርት ሚንስትር ዛሬ ሰኞ አስታውቀዋል።

ለፈተናው ከተቀመጡት 845 ሺሕ 188 ተማሪዎች ውስጥ፣ ያለፉትና ለዩኒቨርስቲ መግቢያ ብቁ የሆነውን 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ያመጡት 27 ሺሕ ብቻ መሆናቸውን የትምሕርት ሚኒስትሩ ፕሮሬሰር ብርሃኑ ነጋ ማስታወቃቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

“ይህም ማለት ፈተናውን ያለፉት 3.2 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው። ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ 0.01 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል” ብለዋል ሚኒስትሩ።

ግማሽ የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች የማለፊያ ነጥቡን ያገኘ ተማሪ እንዳልነበራቸውም ተጠቁሟል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply