የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የአፍሪካ ጉዞ

https://gdb.voanews.com/EA9C5C44-B753-4DA2-833E-56BF56BCAA30_cx0_cy9_cw0_w800_h450.jpg

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ከሚያዝያ 26 እስከ ግንቦት 5/2013 በግብፅ፣ በኤርትራ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ ያደረጉትን የመጀመሪያቸው የሆነውን የሥራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው መመለሳቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

መግለጫው አክሎም “የአፍሪካ ቀንድ በጣም ወሳኝ በሆነ ጊዜ ላይ ነው ያለው” መግለጫ በመጭው ሳምንታት እና ወራት የሚወሰዱ ውሳኔዎች ለአካባቢው ሕዝብ እና እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትስ ጥቅም ላይ ትልቅ አንድምታ ይኖራቸዋል” ብሏል፡፡

“ዩናይትድ ስቴትስ እርስ በእርስ የተሳሰሩትን አህጉራዊ ቀውሶች ለመፍታት እና ዜጎቿ በአስተዳደራቸው ውስጥ ድምፃቸውን የሚያሰሙ እና እንዲሁም መንግስታት ለዜጎቻቸው ተጠያቂ የሚሆኑባት የበለፀገች እና የተረጋጋችን የአፍሪካ ቀንድ ለመደገፍ ቁርጠኛ ናት” ሲል መግለጫው የመንግሥቱን አቋምና የጎዞውን ዓላማ ዘርዝሯል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply