የዩናይትድ ኪንግደም የ70 ዓመታት ንግሥት ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ በ96 ዓመታቸው አረፉ።የ96 ዓመቷ የዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት አረፉ።ንግሥ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/md7sJPk0ZpBYs-sqXCB3jLUQ8uQ2LtshNx9aOqxwTGuK7m8b6tWKykqrEpsJ1dZML2hFaHvGHf8HAO8bAPQDxraMkHv6VHkgyKJJEY7eVdBT1APV_4vTZEABCAeO3nv5VUzQ-RaOy1dgyNqjuMaj-c3mKrHQ8tVGcSSCKm-9zVGo-JU3V-Z1XPwCwfRO4FNWzfwBsMqJPBnMO5odtNSUwqH1EhYmMNQSyiYAgVjh1n43rCNbCmiOsIUgENQbnnaHLQB29LGD2CZywzQ8JaLV00Ot_3RuiJMFgOMijKIGBbG96pPCXVYI5zxo71sPUOaW1dFnoRp76ub5Pb95mRtsgQ.jpg

የዩናይትድ ኪንግደም የ70 ዓመታት ንግሥት ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ በ96 ዓመታቸው አረፉ።

የ96 ዓመቷ የዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት አረፉ።

ንግሥቲቱ ማረፋቸውን የባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት ይፋ አድርጓል።

ቀደም ሲል ሐኪሞች የንግሥቲቱ ጤና በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነው ብለው ነበር።

የንግሥቲቱ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ በርካርታ የንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት ንግሥቲቱ ወደሚገኙበት ስኮትላንድ ባልሞር ቤተ-መንግሥት አቅንተው ነበር።

ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት በ70 ዓመት የንግሥና ዘመናቸው በርካታ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦችን ተመልክተዋል።

የንግሥቲቱን የጤና አሳሳቢ መሆን ዜና  ከተሰማ በኋላ በርካታ ፖለቲከኞች እና ተዋቂ ግለሰቦች በዜናው መረበሻቸውን ሲገልጹ ነበር።

ንግስት ኤልዛቤጥ ወደ ንግስናው የመጡት እአአ 1952 ነበር።

ንግሥቷ በ70 ዓመታት የንግስና ዘመናቸው በዩኬ እና በመላው ዓለም ብዙ ማሕበራዊ ለውጦች ተከናውነዋል።

የንግሥት ኤልዛቤጥ ሞትን ተከትሎ የመጀመሪያ ልጃቸው ቻርልስ የዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመንዌልዝ አገራት ንጉሥ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጳጉሜ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply