
የዩክሬን ድሮኖች በሩሲያ ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ተሰማ፡፡
የዩክሬን የድሮን መሳሪያዎች የሩሲያን የሃይል ተቋማት መምታታቸውን አርቲ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮኖች ዛሬ ማለዳ ላይ በሩሲያ ብራያንስክ ክልል የሃይል ማከማቻ ተቋም ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የአከባቢው ገዥ አሌክሳንደር ቦጎማዝ አረጋግጠዋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በሩሲያ-ዩክሬን ድንበር ላይ በሚገኘው ክሊሞቭስኪ አውራጃ ስልመሆኑ የአካባቢው ገዥ ገልጸዋል፡፡
በአደጋው የሞቱ ወይም ጉዳት የደረሰባቸቸው አካላት ባይኖሩም የሃይል ተቋሙ ሙሉ በሙሉ መጋየቱ ተገልጿል።
በመሳይ ገ/መድህን
ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
Source: Link to the Post