የዮሐንስ አብርሃም ዲፕሎማሲ እና ጆ ባይደን (አሻራ ታህሳስ27፣ 2013ዓ.ም) “ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ስለ ህዳሴ ግድባቡና በኢትዮዽያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ግንዛቤ እንዲኖራቸው አድርጌያ…

የዮሐንስ አብርሃም ዲፕሎማሲ እና ጆ ባይደን (አሻራ ታህሳስ27፣ 2013ዓ.ም) “ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ስለ ህዳሴ ግድባቡና በኢትዮዽያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ግንዛቤ እንዲኖራቸው አድርጌያለሁ” – የጆ ባይደን የሽግግር ቡድን መሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዮሐንስ አብርሃም… ዮሐንስ አብርሃም የባይደንን የሽግግር ቡድን የዕለት ተዕለት ስራ የማስተዳደር ሃላፊነት የተሰጠው ሲሆን የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ የቅርብ ሰውም ነው። ዮሐንስ አበራሐም በጆ ባይደን አስተዳደር ከፍ ያለ ቦታ መያዙ ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስኬት ከፍ ያለ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ከአሁን በፊት የተገለፀ ሲሆን ዮሐንስ የተገመተውን የዲፕሎማሲ ስራዉን ዛሬ ጀምሮታል። ዪሐንስ እንዳለውም ” ግብፆች የነጩን ቤተ መንግስት ጨምሮ መላው አውሮፓ ና አሜሪካውያንን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተዛባ አመለካከት እና አቋም እንዲኖራቸው ያልተጓዙበት መንገድ አልነበረም። በተለይም ዶናልድ ትራምኘ “ግብጽ ግድቡን ልታፈነዳው ትችላለች” እስከማለት እንዲደርሱ ግብፆች የሄዱበት አካሄድ አደገኛ እንደነበር ተረድቼ ነበር። በወቅቱም ስለ ወገኖቼ በጣም አዝኜ ነበር ። ነገር ግን የእኔ ጉዞ ብቻ በቂ ነው ማለት ባልችልም በኢትዮዽያ ወቅታዊ ሁኔታ እና ስለ ህዳሴ ግድቡ የተመለከተ ማብራርያ ለአዲሱ ተመራጭ ፕሬዚደንት ባይደን በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ግንዛቤ እንዲኖራቸው አድርጌያለሁ።” ሲል ተናግሯል። ዮሐንስ አክሎም በየትኛውም የአለም ሀገራት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮዽያውያን እና ትውልደ ኢትዮዽያውያን በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የሚኖሩ ማናቸውም ኢትዮዽያዊያን ጋዜጠኞች፣ ተንታኞች፣ ፀሀፊዎች የሀገራቸው ህልውና ስለሆነው የህዳሴ ግድብ በተመለከተ ለሚቀርባቸው የውጭ ዜጋ ሁሉ በቂ መረጃ በመስጠት የግብፃችን ሴራ የማክሸፍ ስራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል!! ጋዜጠኛ እስሌማን ዓባይ እንደዘገበው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply