የደህንነትና መረጃ አገልግሎት ባልደረባ የሆኑና የመንግስት ሚስጥርን ለህወሃትና ለኦነግ ታጣቂዎች አሳልፈው ሲሰጡ የነበሩ 222 የተቋሙ ሰራተኞችን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡…

የደህንነትና መረጃ አገልግሎት ባልደረባ የሆኑና የመንግስት ሚስጥርን ለህወሃትና ለኦነግ ታጣቂዎች አሳልፈው ሲሰጡ የነበሩ 222 የተቋሙ ሰራተኞችን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡…

የደህንነትና መረጃ አገልግሎት ባልደረባ የሆኑና የመንግስት ሚስጥርን ለህወሃትና ለኦነግ ታጣቂዎች አሳልፈው ሲሰጡ የነበሩ 222 የተቋሙ ሰራተኞችን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡ // አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-22/03/13/ዓ.ም //… በተጨማሪም ለትህነግ እና ኦነግ የፋይናንስ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ 69 ባለሀብቶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረጉ ሲሆን የ23ቱ ባለሃብቶች ነዋሪነታቸው በተለያዩ የክልል ከተሞች ሲሆን 46ቱ ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ መሆናቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ሥም ዝርዝራቸውን መግለፅ በአንድ ብሄር ላይ ያነጣጠረ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዳይመስል በማለት የመረጃ ምንጫችን የባለሀብቶቹን ስም ዝርዝር ከመጥራት ተቆጥቧል፡፡ ሁለቱን የጥፋት ድርጅቶች በገንዘብ ሲደግፉ እንደነበር ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ሥር የዋሉት 69ኙ ታላላቅ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ታዋቂ የሆኑ በሆቴል አገልግሎት እና አምራች ፋብሪካዎች ባለቤቶች ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ባለሀብቶች የአንድ ብሄር ተወላጆች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በመቀሌ ከተማ በሚገኘው የአሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በሚገኙ አንደርግራውንድ ቤቶች ውስጥ 92 የሞቱ ሰዎች አስክሬንም ተገኝቷል፡፡ የ23ቱ ሰዎች አስክሬን በቅርብ ግዜ ውስጥ እንደሞቱ እና ቀሪዎቹ ደግሞ ረዘም ላለ ግዜ የቆዩ አስክሬኖች መሆናቸውን የመረጃው ምንጫችን ጠቁሟል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply