የደም ባንክ ከፍተኛ የደም እጥረት ገጥሞኛል አለ፡፡

ከወቅታዊ አገራዊ ችግር ጋር በተያያዘ በከፍተኛ መነቃቃት በርካቶች ደም ቢለግሱም ደም በባህሪው ረጅም ጊዜ የሚቆይ ባለመሆኑ በአሁኑ ሰዓት እጥረት ገጥሞኛል ሲል የብሔራዊ ደም ባንክ አስታውቋል፡፡በተለይም ከካንሰር እና የደም አለመርጋት ችግር ላለባቸው ህሙማን የሚያገልግለው ፕላትሌት የተሰኘው የደም ዓይነት የቆይታ ጊዜው አጭር በመሆኑ ህብረተሰቡ በቋሚነት ደም እንዲለግስ የደም ባንኩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ያረጋል ባንቴ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

ደም ባንኩ በቋሚነት በመንግስት ተቋማት ውስጥ ወቅቱን የጠበቀ የደም ልገሳን ቢያከናውንም ከኮቪድ መከሰት በኋላ የለጋሾች ፍላጎት መቀነሱን ባንኩ አስታውቋል፡፡ህብረተሰቡ ወቅታዊ ክስተትን ተከትሎ በመነቃቃት መለገሱ እና በሌላ ጊዜ ቸልተኛ መሆኑ አሰራራቸውን እንዳዛባባቸው የባንኩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ያረጋል ባንቴ አስታውቀዋል፡፡

ቀን 14/ 03/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply