የደረት ህመም (Chest pain)

ብዙ ሰዎች የደረት ህመም ወይም ጨምድዶ የመያዝ እና የመውጋት ስሜት ያጋጥማቸዋል ።
የደረት ህመም በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት እንደሚችልም ባለሙያዎቸ ይናገራሉ፡፡
የደረት ህመም ከቀላል ህመም ህይወትን አደጋ ላይ እስከ ሚጥል ችግር ሊያስከትል እንደሚችልም ያስረዳሉ፡፡
ይህ ችግር ከጥቂት ደቂቃዎች እስከ በርካታ ቀናት ሊቆይ እንደሚችልም ይነሳል፡፡
ታድያ በዚህ ጉዳይም ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ጣቢያችን የልብ እስፔሻሊስት ሀኪም ከሆኑት ዶ/ር አብዱሰመድ አደም ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

የደረት ህመም ምንድን ነው ?

የደረት ህመም ብዙ አይነት ናቸው በብዙ ምክንያትም ይመጣል ይላሉ ባለሙያው፡፡
ለምሳሌ ደረት ላይ የመውጋት ባህሪ የህመም አይነት ፣ትንፋሽ የማሳጠር፣ደረትን ጨምቆ የመያዝ ፣ ዝምብሎ የመውጋት ባህሪ ያላቸው የደረት ህመሞች አሉ፡፡
እንዲሁም ከእንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ፣አየር ወደ ውስጥ ስናስገባ የሚመጣ የደረት ህመሞች መኖራቸውን ተናግረዋል።

የደረት ህመም መንስኤዎች

 • የልብ ህመም
 • በሳንባ ምክንያት የሚመጣ የደረት ህመም
 • ደረታችል ላይ ባለ ጡንቻ ምክንያት እና የአጥንት ህመም ይጠቀሱበታል።
  እነዚህም የሚለዮበት መንገድ በልብ ምክንያት የሚመጣ የደረት ህመም እንቅስቃሴን ተከትሎ ይመጣል፡፡በሳንባ ምክንያት የሚመጣ የደረት ህመም አየር መምናስገባበት ግዜ ይመጣል፡፡

የሚታዩ ምልክቶች

 • በልብ ምክንያት የሚመጣ የደረት ህመም ስሜቱ ወደ አንገት ፣ትከሻ፣እጅ እና አገጭ የመሄድ ባህሪ አለው፡፡
 • በሳምባ ምክንያት የሚመጣ የደረት ህመም አየር ወደ ውስጥ ሲሳብ ይወጋና ትንፋሻችንን እንዳንጨርስ ማድረግ
 • ደረታችን ላይ ባሉ ጡንቻዎች የሚመጣ ከሆነ የጡንቻዎች አካባቢ ህመም ይኖራል።
  አንዳንዴ እነዚህ ምልክቶች ሊቀላቀሉ እንደሚችሉም ዶ/ር አብዱሰመድ ተናግረዋል፡፡
  ችግሩን ለመከላከልም የደረት ህመምን የሚያመጡትን ነገሮች ለይቶ ማወቅ እንደሚያስፈልግ እና ችግሩ ወደ ከፋ ደረጃ ሳይደርስ ወደ ህክምና ተቋም ሄዶ መታየት እንደሚመረጥ አንሰተዋል፡፡

የሚደረጉ ህክምናዎች

 • ኢሲጂ ማንሳት
 • የልብ አልትራሳውንድ ማንሳት
 • ሲቲስካን ማንሳት
 • የደረት ራጅ

በመጨረሻም የደረት ህመም የሚሰማቸው ሰዎች ችግሩ ሳይባባስ ወደ ህክምና ተቋም ሄደው ተገቢውን ህክምና ማግኘት እንደሚያስፈልግ ዶ/ር አብዱሰመድ ተናግረዋል፡፡

በሐመረ #ፍሬው

መጋት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply