የደሴ ሆስፒታል ማከም ጀመረ

የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀለል ያሉ የህክምና አገልግሎቶችን መስጠት መጀመሩ ተገለፀ።

የሰማንያ ዓመታት ዕድሜ ያለው ይህ ሆስፒታል “የህወሓት ታጣቂዎች ውድመትና ዘረፋ አድርሰውበታል” ከተባለ በኋላ አሁን የህክምና አገልግሎት የሚሰጥባቸው የራሱ መሣሪያዎች እንደሌሉት የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ኃይማኖት አየለ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ቀለል ያሉ አገልግሎቶችን መስጠት የተጀመረው በሃኪሞቹ ልምድና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ጋር በመተጋገዝ  መሆኑንም ሥራ አስኪያጇ አመልክተዋል።

“ታጣቂዎቹ ሲቪሎችንና ሲቪል ተቋማትን ዒላማ አድርገዋል” በሚል የሚቀርቡባቸውን ክሶችን የህወሓት መሪዎች ሲያስተባብሉ ቢቆዩም የአማፂው ኃይሎች በአማራ ክልል በቆዩናቸው አካባቢዎች አርባ ሆስፒታሎችንና 453 የጤና ጣቢያዎችን ጨምሮ በርካታ የጤና ተቋማትን ማውደማቸውንና ዘረፋ መፈፀማቸውን” የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ ገልፀዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply