የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የድንገተኛ ማዋለድ እና ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በከፊል ሥራ ጀመረ የአማራ ሚዲያ ማእከል ታህሳስ 8 2014 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የድንገተኛ…

የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የድንገተኛ ማዋለድ እና ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በከፊል ሥራ ጀመረ የአማራ ሚዲያ ማእከል ታህሳስ 8 2014 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የድንገተኛ ማዋለድ እና ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በከፊል ሥራ እንዲጀምር ማድረጉን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ገለጸ፡፡ ኮሌጁ በጤና ሚኒስቴር በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት በአሸባሪው ህወሓት ከፍተኛ ውድመት የደረሰበትን የደሴ አጠቃላይ ሆስፒታል ወደነበረበት ለመመለስና አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ለዚህም ከፍተኛ ስፔሻሊሰት፥ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞች፣ ነርሶችና እና ሌሎችን የጤና ባለሙያዎች ያካተተ የሕክምና ቡድን በስፍራው ማስማራቱን ነው ኮሌጁ የገለጸው፡፡ በአሁኑ ወቅትም የድንገተኛ የማዋለድ አገልግሎት እና የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በከፊል ማስጀመር መቻሉን ከኮሌጁ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ሆስፒታሉ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ሰፈውን አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡ ለሆስፒታሉ አስፈላጊ የሕክምና ቁሳቁሶችን እና መድሐኒቶችን በማሟላት መደበኛ አገልግሎቱ እንዲጀምር ይደረጋልም ነው የተባለው፡፡ የአሸባሪው ህወሃት ወራሪ ቡድን የደሴ ሪፈራል ሆስፒታልን ሙሉ ለሙሉ ከመዘርፉም በላይ መውሰድ የማይችለውን ደግሞ አውድሟል፡፡ የሆስፒታሉ ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው መታፈሪያ ቀደም ሲል እንስታወቁት÷አሸባሪ ቡድኑ ስብዓዊ አገልግሎትና ህይወት የማዳን ስራ እየሰራ ባለው የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል። የአሸባሪው ወራሪ ሃይል የሆስፒታሉን መድሃኒት እና የኦክስጅን ማምረቻ ጨምሮ ግዙፍ የህክምና ማሽነሪዎችን ማምረቻ ሙሉ ለሙሉ ዘርፏል የማይችለውንም አውድሟል። ለሆስፒታሉ የሚያስፈልግ ድጋፍ ለማድረግ የሚፈልግ በ 976 በመደውል መረጃ ማግኘት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ FBC እንደዘገበው

Source: Link to the Post

Leave a Reply