የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የማዕከል ከተማ መረጣ አለመግባባት

https://gdb.voanews.com/03a3032a-1728-4b5d-acd5-783bd952235a_tv_w800_h450.jpg

አዲስ በሚመሠረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዋና ከተሞች አመራረጥ ላይ ቤንች-ሸኮ ዞን ቅሬታ አሰምቷል።

ክልሉን ለመመሥረት በህዝብ ድምፅ ከወሰኑት አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ አንዱ የሆነው የቤንች-ሸኮ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ “የዋና ከተማው ምርጫ በገለልተኛ አካል ውሳኔ ሳይደረግበት ክልል ሊመሠረት አይገባም” ብለዋል።

የቤንች-ሸኮ ምክር ቤት በበኩሉ ትናንት/ረቡዕ/ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ላይ እስካሁን የነበረው አሠራር ህግና ሥርዓትን የተከተለ እንደነበር አመልክቶ ዋና ከተማን በሚመለከት ቀድም ሲል በተቀመጠው የጋራ ስምምነት መሠረት በገለልተኛ አካል በሚወጣ መስፈርት እንዲፈታ፤ እስከዚያ ግን የክልሉ ምሥረታ እንዲራዘም ጠይቋል።

የክልሉ ምሥረታ አጠቃላይ ጉዳዮች በጥንቃቄ ሲሠራባቸው መቆየቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ውሳኔ ህዝብ ማስፈፀሚያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምትኩ በድሩ ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply