የደቡብ አፍሪካው ምክር ቤት ቃጠሎ ተጠርጣሪ ፍ/ቤት ቀረበ

ባላፈው ዕሁድ በደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት ህንጻ ላይ ለደረሰው የእሳት አደጋ ተጠርጥሮ የተከሰሰው የ49 ዓመቱ ዛንዲሌ ክሪስመስ ማፌ ዛሬ ማክሰኞ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡ 

ማፌ የተከሰሰው የእሳት ቃጠሎ በማድረስ፣ ሰብሮ በመግባትና በስርቆት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ፣ ተጠርጣሪው ማፌ፣ በእጁ ከነበረው ተቀጣጣይ ፈንጂ፣ ሰርቋቸዋል ከተባሉት ላፕቶፖችና ሰነዶች ጋር መያዙን አስታውቋል፡፡ የማፌ ጠበቃ ተከሳቹ ጥፋተኛ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

በተቃጣጣይ ነገሮችና ፈሳሾች ጭምር እየታገዘ የደረሰው ቃጠሎ፣ የ138 ዓመት ታሪክ ያለው የደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት ህንጻን ጨምሮ፣ በአካባቢው በሚገኙ ሌሎች የአዲሱን ምክር ቤት ህንጻዎች ማቃጠሉ ተመልክቷል፡፡ 

Source: Link to the Post

Leave a Reply