የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ለኮቪድ-19 ተጋለጡ

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ስሪል ራሞፎሳ ትናንት እሁድ በተደረገላቸው ምርመራ ለኮቪድ-19 ቫይረሰ የተጋለጡ መሆናቸው ተነገረ፡፡

ፕሬዚንዳንቱ የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ደክለርክ ቀብር ላይ በኬፕ ታወን ከተገኙ በኋላ መጠነኛ የህመም ስሜት የተሰማቸው ቢሆንም አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆኑን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ 

የ69ኛ ዓመቱ ራማፎሳ በሚቀጥለው ሳምንት ለጊዜው ራሳቸውን ከአስተዳደራዊ ሥራቸው አግልለው ኃላፊነታቸውን ለምክትል ፕሬዚዳንት ዴቪድ ሙባዛ ያስተላለፉ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡ 

ባሁኑ ወቅት በደቡብ አፍሪካ በክፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ የሚገኘው የኦሚክሮን ቫይረስ በቀን ወደ 20 ሺ በሚጠጉ ሰዎች ላይ እየታየ መሆኑን በዘገባው ተመልክቷል፡፡  

ይሁን እንጂ የደቡብ አፍሪካ ሳይንቲስቶች ቫይረሱ ከፍተኛ ህመም ሲፈጥር ያልተመለከቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply