የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተወሰነ

የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ወደ እስር ቤት እንደሚለሱ በትናንትናው እለት ትዕዛዝ መስጠቱ ተገለጠ፡፡

የ79 ዓመቱ ዙማ ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ የተደረጉት ባለፈው መስከረም በህክምና ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ በውጭ እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ መሆኑም ተገልጿል፡፡ 

የቀድሞው ፕሬዚዳንት፣ የሙስና ወንጀልን ለመመርመር በተሰየመው አካል ፊት እንዲቀርቡ፣ ፍርድ ቤቱ የሰጣቸውን ትዕዛዝ ባለማክበራቸው፣ ፍርድ ቤቱን ተዳፍረዋል በሚል፣ የ15 ወራት እስር የተፈረደባቸው መሆኑን ይታወቃል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply