የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ 11ኛ ክልል የስልጣን ርክክብ ለማድረግ ለነገ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራየደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የስልጣን ርክክብ ለማድረ…

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ 11ኛ ክልል የስልጣን ርክክብ ለማድረግ ለነገ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የስልጣን ርክክብ ለማድረግ ነገ ጥቅምት 24 2014 አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ተገልጿል።

በደቡብ ክልል ስር የነበሩ አምስት ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ የራሳቸውን የጋራ ክልል ለመመሰረት የሚያስችላቸውን ህዝበ ውሳኔ ያካሄዱት ባለፈው መስከረም 20 2014 ነበር።

በዕለቱ ድምጽ ለመስጠት ከወጡ 1,262,679 የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል 96 በመቶው የአዲሱን ክልል መመስረት መደገፋቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

ምርጫ ቦርድ የህዝበ ውሳኔውን ውጤት ለፌደሬሽን ምክር ቤት በደብዳቤ ባሳወቀው መሠረት ጥቅምት 20 2014 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የህዝበ ውሳኔውን ውጤት ማፅደቁ ይታወሳል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል 11ኛው ክልል መሆኑ የሚረጋገጥበት ይሆናል ተብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply