የደቡብ ክልል አደረጃጀት ዙሪያ የቀረበው ሰነድ ተቃውሞ ገጠመው

https://gdb.voanews.com/09680000-0a00-0242-4ca7-08da6b363dca_tv_w800_h450.jpg

የደቡብ ክልል አደረጃጀት ጥያቄዎች ላይ ለመወሰን ሕዝቡ እንዲወያይበት የቀረበው የኩታ ገጠም ወይም የክላስተር አደረጃጀት ሰነድ «ኢ – ሕገ መንግስታዊ» ሲል የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መቃወሙን የንቅናቄው ሊቀመንበር  ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

“የክልልነት ጥያቄዎችን በተመለከተ፣ አዲስ ክልሎች የሚመሰረቱት ሕህዝብ ፍላጎት ብቻ ነው” ሲሉለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ ለዚህ ሲባል በየአካባቢው ውይይት መጀመሩን አመልክተዋል።

ቪኦኤ ያነጋገራቸው ምሁራን በበኩላቸው የክልሉ መንግሥት በቀረው የደቡብ ክልል ዕጣ ፈንታ ላይ የጠራ አቋም አለማሳየቱን ገልፀው መፍትሄው “ሕዝብ ውሳኔ” አልያም አሁን ሥራ ላይ ያለውን የአገሪቱና የክልሉን ሕገ መንግስት ማሻሻል ነው ብለዋል።

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

Source: Link to the Post

Leave a Reply