የደቡብ ክልል የዚህ አመት የተፈጥሮና አካባቢ ጥበቃ የህብረተሰብ ተሳትፎ ንቅናቄ ጥር 18 ይጀመራል

የደቡብ ክልል የዚህ አመት የተፈጥሮና አካባቢ ጥበቃ የህብረተሰብ ተሳትፎ ንቅናቄ ጥር 18 ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል የዚህ አመት የተፈጥሮና አካባቢ ጥበቃ የህብረተሰብ ተሳትፎ ንቅናቄ ከጥር 18 ቀን 2013ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት እንደሚካሄድ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።
ለዚህም ከ 5 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የሰው ሀይል ልየታ እና አስፈላጊ ግብአቶች መዘጋጀታቸውንም ቢሮው አስታውቋል፡፡
በክልሉ የተፋሰስ ልማትም 3 ሺህ 884 ነባርና አዳዲስ ንዑስ ተፋሰሶች እንደሚለሙም ተገልጿል፡፡
በዘንድሮው ዓመት ንቅናቄ በተለይም በሀይል ማመንጫ ግድቦች አካባቢ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ለመስራት ግብ ተይዟል ነው የተባለው፡፡
በባለፈው አመት በተካሄደ የተፋሰስ ልማት ስራ 355 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ስነ አካላዊና ስነ ህይወታዊ ስራዎች መሰራታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የደቡብ ክልል የዚህ አመት የተፈጥሮና አካባቢ ጥበቃ የህብረተሰብ ተሳትፎ ንቅናቄ ጥር 18 ይጀመራል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply