የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በዳንሻ ሁመራና ወልቃት ለሚገኙ የአማራ ልዩ ሀይልና የሚሊሻ አባላት ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍን ይዞ ወደ ስፍራው ማቅናቱ ተገለ…

የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በዳንሻ ሁመራና ወልቃት ለሚገኙ የአማራ ልዩ ሀይልና የሚሊሻ አባላት ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍን ይዞ ወደ ስፍራው ማቅናቱ ተገለፀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የትህነግ ጁንታ ቡድን በራሱ ተንኳሽነት በጀመረው ጦርነት የአማራ ልዩ ሀይልና የሚሊሻ አባላት ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ታላቅ ድል ተመዝግቧል፡፡ ለዚህ ተጋድሏቸው ከጎናቸው በመሆን በማበረታታት የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደርና ማህበረሰቡ በርካታ ልዩ ልዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል። በዛሬው እለት በደቡብ ጎንደር ዞን ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ከሴቶች ሊግ፤ፌደሬሽንና ሴቶች ማህበራት፤ከደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ፤ከአዲስ ዘመን ሆስፒታል ተውጣጥቶ የተዘጋጀ 196 ኩንታል ዳቦ ቆሎ፤ቆሎ 42.5 ኩንታል፤በሶ 112.5 ኩንታል፤ድርቆሽ 67.5 ኩንታል፤መኮረኒ 11 ኩ፤ስኳር 19.5 ኩ፤204 ደርዘን ው፤50 ደርዘነረ ጁስ፤እና 166 ደርዘን ደርዘን ብስኩት ወደ ቦታው ተጭኖ ተልኳል፡፡ ድጋፉን ለማስረከብ ከተሳተፉ አካላት መካከል የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ አመራሮች፤የሎጅስቲክ ኮሚቴዎች፤የወረዳና ከተማ አስተዳደር፤እንዲሁም የደብረታቦር የኒቨርስቲ ተወካዮች ናቸው። የድጋፉ አላማም በቦታው ተገኝቶ የአካባቢውን የመልሶ መቋቋምና ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወኑ የሚገኙ የጸጥታ አካላትን በመደገፍ መላ ህዝቡን ፤አመራሩን ለማበረታታትና በቀጣይ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ እንዲያመች ያለመ ስለመሆኑ ተገልጧል ሲል የደቡብ ጎንደር ዞን የመ/ኮ/ጽ/ቤት ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply