You are currently viewing የደባርቅ ከተማ አስተዳደር 16 ሰርገው የገቡ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ነሃሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ የህይወ…

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር 16 ሰርገው የገቡ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የህይወ…

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር 16 ሰርገው የገቡ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የህይወትን እኩይ ዓላማ ለማስፈፀም በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማዋ ገብተው እየተንቀሳቀሱ የመረጃ ማቀበል ስራ የሚሰሩ 16 ተጠርጣሪ ሰርጎ ገቦችን እና ሶስት ህገ-ወጥ መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደባርቅ ከተማ ከንቲባ እና የፀጥታ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ብርሀን ፀጋየ ገልፀዋል። የህወሀትን ዳግም ወረራ ለመከላከል በሚደረግ ዘመቻ የመጀመሪያው ተግባር ከተማዋን ከሰርጎ ገብ መጠበቅ እና የደጀንነት ሚናን መወጣት ዋነኛና ቁልፍ ተግባር መሆኑ ተመላክቷል። ደባርቅ ከተማ ውስጥ በጠንካራ የመረጃ መዋቅር እና የኬላ ጥበቃ እና በሌሎች ስምሪቶች የህወሀት ተላላኪ ሰርጎ ገብ ዓላማውን እንዳያሳካ የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል ተብሏል። የደባርቅ ከተማ ባለገጀራ ወጣቶች ፣ የሰሜን ጎንደር ጥቁር አንበሳ የቀድሞ ሰራዊት የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር አባላት ፣ አጠቃላይ የፀጥታ መዋቅሩ ፣ ወጣቶችና ማህበረሰቡ የአካባቢውን ሰላም እያስጠበቀና የደጀንነት ተግባር እየፈፀመ እንደሚገኝ የደባርቅ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮምንኬሽን መረጃ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply